Loading
አዝ፦ እንደተናገረን ፡ አደረገው አወራለሁ ፡ እኔ ፡ ባይኖቸ ፡ ስላየሁ ዘምራለሁ ፡ እኔ ፡ እመሰክራለሁ (፪x) ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ምሥጋናችን ፡ ይሄው ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ለኛ ፡ ያደረገው ፩) ተረስተናል ፡ እኛ ፡ አንቅም ፡ ብለን ጉድጓድ ፡ ለኛ ፡ ጠልቋል ፡ ስንል ፡ አበቃልን የተስፋ ፡ ቃል ፡ ኪዳን ፡ የሰጠን ፡ እግዚአብሔር ባይናችን ፡ አየነው ፡ ሲያወጣን ፡ በክብር (፪x) አዝ፦ እንደተናገረን ፡ አደረገው አወራለሁ ፡ እኔ ፡ ባይኖቸ ፡ ስላየሁ ዘምራለሁ ፡ እኔ ፡ እመሰክራለሁ (፪x) ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ምሥጋናችን ፡ ይሄው ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ለኛ ፡ ያደረገው ፪) ጠላት ፡ በሩጫችን ፡ ፍላጻን ፡ ወርውሮ ያሰብነውን ፡ ስናይ ፡ ሊያስቀረን ፡ ሞክሮ በሳት ፡ በደመና ፡ የታደገን ፡ ጌታ ፍላጻን ፡ ሰበረ ፡ ሆነልን ፡ መከታ (፪x) አዝ፦ እንደተናገረን ፡ አደረገው አወራለሁ ፡ እኔ ፡ ባይኖቸ ፡ ስላየሁ ዘምራለሁ ፡ እኔ ፡ እመሰክራለሁ (፪x) ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ምሥጋናችን ፡ ይሄው ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ለኛ ፡ ያደረገው ፫) አይችልም ፡ አትበሉ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይችላል ኤልሻዳይነቱን ፡ ታሪክ ፡ ይናገራል ባሳለፍነው ፡ ጊዜ ፡ እኛም ፡ አይተነዋል ያለውን ፡ አድራጊ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ብለናል (፪x) የተስፋ ፡ ቃሉን ፡ ፈጸመው አዝ፦ እንደተናገረን ፡ አደረገው አወራለሁ ፡ እኔ ፡ ባይኖቸ ፡ ስላየሁ ዘምራለሁ ፡ እኔ ፡ እመሰክራለሁ (፪x) ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ምሥጋናችን ፡ ይሄው ልዩ ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ለኛ ፡ ያደረገው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.