Loading
ያለፍነውን ፡ ያሳለፈን ፡ አረማነው ዮርዳኖስን ፡ የከፈለው ፡ አረ ፡ ማነው ማነው (፪x) ፡ አረማነው (፪x) እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብርቱ ፡ ሃያል እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ በሰልፍ ፡ ኃያል (፪x) ፩) ኃጢአታችን ፡ እጅግ ፡ በዝቶ ነፍሳችንን ፡ አስጨንቆ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በኛ ፡ አዝኖ ሀይወታችን ፡ ተበላሽቶ የተቤዥን ፡ በምህረቱ ፡ ያስታረቀን ፡ ከአባቱ የዘላለም ፡ ጠባቂያችን ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ እረኛችን እንደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ለዘላለም የሚችለን ፡ ማንም ፡ የለም ፪) በባዕድ ፡ ምድር ፡ ስንጨቆን ስንገዛ ፡ በፈርኦን መከራችን ፡ የተሰማው ሃዘናችን ፡ ያሳዘነው እስራትን ፡ የሰበረ ፡ ቀንበሩንም ፡ የሰበረ ባለድሎች ፡ ያደረገን ፡ መልካም ፡ ነገር ፡ ያጠገበን እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ለዘላለም የሚረዳን ፡ ማንም ፡ የለም ፫) የእኛን ፡ መውደቅ ፡ የተመኙ ጉድጓዳችንን ፡ የቆፈሩ በእጃቸው ፡ ተንኮል ፡ ይዘው ወጥመዶችን ፡ ለእኛ ፡ አጥምደው ዛሬ ፡ ነገ ፡ ጠፋ ፡ ያለ ፡ የኛን ፡ ረዳት ፡ ያላወቁ እጃቸውን ፡ በአፋቸው ፡ አድርገዋል ፡ በስራቸው እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ለዘላለም የሚያጸናን ፡ ማንም ፡ የለም
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.