Loading
የበግ ፡ መንጋ ፡ ስጠብቅ ስሙን ፡ በዜማ ፡ ሳደንቅ ልዑል ፡ አየና ፡ ከሰማይ ልቡ ፡ አረፈ ፡ በእኔ ፡ ላይ እንዴት ፡ ያለ ፡ ዓይን ፡ አለው (፪x) ከሰው ፡ ልጆች ፡ ልዩ ፡ ነው ሃሌሉያ (፫x) ደካማነቴንም ፡ አውቆ አንበሳውን ፡ ለእኔ ፡ ለቆ ጠላቴ ፡ ብዙ ፡ ሲሞክር መጋጋውን ፡ ሰባብሮ የረዳኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) በዝማሬ ፡ ላመስግነው ሃሌሉያ (፫x) ሀይልንም ፡ የሚያስታጥቀኝ መንገዴንም ፡ የሚያቀና አጽንቶ ፡ የሚያቆመኝ ጠላቴንም ፡ የሚረታ በአማላክት ፡ መካከል እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው ክብሬ ፡ ትዘምርለት ማዳኑ ፡ ለልጅ ፡ ልጅ ፡ ነው ሃሌሉያ (፫x) በሥጋ ፡ ታናሽ ፡ ብመስልም ጐልያድ ፡ በእኔ ፡ ቢስቅም የታመንኩበት ፡ ጌታ ፡ ነው በጠጠር ፡ የሚዘረጋው እኩያ ፡ አቻ ፡ የሌለው ብርቱ ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) ሃሌሉያ (፫x) ተመስገን (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.