Loading
አሻግረኸናል ፡ ባሕሩን ከፍለህልናል ፡ ውሃውን ፈታችን ፡ ሆነህ ፡ ስትመራን ማንም ፡ አልቻለም ፡ ሊያቆመን አረ ፡ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ በሰማይ ማን ፡ ነው ፡ ይፈለግ ፡ የበላይ ምድርና ፡ ሞላው ፡ ያንተ ፡ ነው ለሕዝብ ፡ ሞገስ ፡ የሆንከው ችግራችን ፡ የአንተ ፡ ችግር ሃዘናችን ፡ የአንተ ፡ ሀዘን ነበር ፡ ለካ ፡ የኛ ፡ ጌታ ምትክ ፡ ሆንከን ፡ በኛ ፡ ፈንታ እስከ ፡ መስቀል ፡ ወደድከን ከሞት ፡ ወደ ፡ ሕይወት ፡ ተሻገርን ተሸከምነው ፡ የኛን ፡ በደል ፡፡ለዘላለም ፡ ኢየሱስ ፡ ክበር (፪x) ስንደክም ፡ ስትበረታ ስንወድቅ ፡ ሲታገለን ማን ፡ ነው ፡ እንዳንተ ፡ የቻለን አለሁ ፡ ያለ ፡ ያልታዬን ወረት ፡ ከቶ ፡ የማያውቅ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ተባረክ (፬x) ሆድ ፡ ሲብሰን ፡ ይገባሃል ብሶታችን ፡ ይሰማሃል ከስትንፋስ ፡ ይልቅ ፡ ቅርብ ፡ ነህ ለእኛ ፡ አንተ ፡ ታስባለህ ከናት ፡ በላይ ፡ አሳዳጊ ትዕግሥተኛና ፡ አሳላፊ የተጐዳን ፡ አስታማሚ ሰው ፡ አድርጐ ፡ ለክብር ፡ ሿሚ ባሕሩ ፡ ሲቆም ፡ ፊታችን ፈርኦን ፡ ሲሮጥ ፡ ኋላችን አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኛ ፡ የደረስክ ውሃውን ፡ ለሁለት ፡ የከፈልክ ልባችን ፡ በአንተ ፡ አረፈ አሳዳጃችን ፡ አፈረ መርጦናል ፡ ባንተ ፡ መደገፍ በምንም ፡ ነገር ፡ ብናልፍ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.