Loading
ምርኩዜ ሸንበቆ መች ሆነና ተሰብሮ ሚወጋኝ እንደገና የዘላለም አምባ መኖሪያዬ በአምላክ ጥላ ስር ነው ማረፊያዬ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ(×፪) እኔስ ባንተ ጌታዬ እመካለሁ እኔስ ባንተ ኢየሱሴ እመካለሁ የሚደገፍ በእግዚአብሔር ይደገፍ(×፪) እኔስ ባንተ እደገፋለሁ(×፪) የጌታዬ ሀሉን እያየሁኝ ትምክህቴ በዛ በረታሁኝ በእሳት የሚመልስ የታወቀ የአባቾቼ አምላክ ከጎኔ ነው የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ(×፪) እኔስ ባንተ ጌታዬ እመካለሁ እኔስ ባንተ ኢየሱሴ እመካለሁ የሚደገፍ በእግዚአብሔር ይደገፍ(×፪) እኔስ ባንተ እደገፋለሁ(×፪) ጌታዬ ስጠራው መቼ ዘገየ ጠላቶቼ አለቁ አይኔ እያየ እኔ ግን በክብር ተሻገርኩኝ የእግዚአብሔርን ክንዱን እያየሁኝ ጌታዬ ስጠራው መቼ ዘገየ ተራራው ተናደ አይኔ እያየ ጌታዬ ስጠራው መቼ ዘገየ ማድጋዬ ሞላ አይኔ እያየ ጌታዬ ስጠራው መቼ ዘገየ ተራራው ተናደ አይኔ እያየ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ(×፪) እኔስ ባንተ ጌታዬ እመካለሁ እኔስ ባንተ ኢየሱሴ እመካለሁ የሚደገፍ በእግዚአብሔር ይደገፍ(×፪) እኔስ ባንተ እደገፋለሁ(×፪)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.