Loading
አመልካለሁ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ ጥያቄዬን ፡ ሁሉ ፡ እረስቼ ዓላማዬ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ከቶ ፡ አልሄድም ፡ ክበር ፡ ሳልልህ ዓላማዬ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ከቶ ፡ አልሄድም ፡ ክበር ፡ ሳልልህ (፪x) ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x) ሁልጊዜ ፡ ሥምህን ፡ እጠራለሁ ፡ እጠራለሁ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ እልሃለሁ ፡ እልሃለሁ (፪x) እልሃለሁ ፡ እልሃለሁ ፣ እልሃለሁ ፡ እልሃለሁ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x) እንደ ፡ ማር ፡ ጣፈጠኝ ፡ ሥምህ ፡ አፌ ፡ ላይ ከሥምህ ፡ የሚበልጥ ፡ ሥም ፡ ይገኛል ፡ ወይ (፪x) ሥሞች ፡ ተሰብስበው ፡ ለሥምህ ፡ ሰገዱ ከሥማቸው ፡ ይልቅ ፡ ሥምህን ፡ ወደዱ (፪x) ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x) ምስጢሩ ፡ ምንድን ፡ ነው ፡ ምስጢሩ ፡ ይኼ ፡ ነው ሥሙን ፡ ያስወደደው ፡ በሃሪው ፡ እኮ ፡ ነው (፪x) ሥሙና ፡ ሕይወቱ ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ይሄዳል እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ ከወዴት ፡ ይገኛል (፪x) ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x) እሺ ፡ ባይነትህ ፡ ታዛዥነትህ ክብርህን ፡ ለመጣል ፡ ክብር ፡ መጣልህ (፪x) ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ማለትህ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አድርጐሃል ከሥሞች ፡ የሚበልጥ ፡ ሥምን ፡ አሰጥቶሃል (፪x) ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x) አመልካለሁ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ ጥያቄዬን ፡ ሁሉ ፡ እረስቼ ዓላማዬ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ከቶ ፡ አልሄድም ፡ ክበር ፡ ሳልልህ ዓላማዬ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ከቶ ፡ አልሄድም ፡ ክበር ፡ ሳልልህ ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ (፬x) ምነው ፡ ነፍሴ ፡ እንደ ፡ ውኃ ፡ በሆንልኝ አምላኬ ፡ ፊት ፡ እንደ ፡ ጅረት ፡ ቢፈስልኝ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.