Loading
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር ንጹህ ፡ ፍፁም ፡ ነውር ፡ የሌለህ (፪x) አንተ ፡ ነውር ፡ የለህም አንተ ፡ እድፈት ፡ የለህም አንተ ፡ ጉድለት ፡ የለህም አንተ ፡ እንከን ፡ የለህም (፪x) አንተ ፡ ራስህ ፡ እውነት ፡ ነህ ምንም ፡ ውሸት ፡ የለብህ ኦ ፡ የለብህ (፪x) ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር ንጹህ ፡ ፍፁም ፡ ነውር ፡ የሌለህ (፪x) አንተ ፡ ነውር ፡ የለህም አንተ ፡ እድፈት ፡ የለህም አንተ ፡ ጉድለት ፡ የለህም አንተ ፡ እንከን ፡ የለህም (፪x) ታድያ ፡ እኔ ፡ ተስፋዬ ፡ ማነው እግዚአብሔር ፡ አይደለም ፡ ዎይ (፪x) አሁንስ ፡ ተስፋዬ ፡ ማነው እግዚአብሔር ፡ አይደለም ፡ ዎይ (፪x) ጠቢብ ፡ በጥበቡ ፡ አይመካ ኃያልም ፡ በኃይሉ ፡ አይመካ ፍርድንና ፡ ጽድቅን ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ የሚያደርግ እርሱ ፡ መሆኑን ፡ በማወቁ ፡ ብቻ በዚያ ፡ ይመካ (፪x) አውቄያለሁና ፡ ጠንቅቄ ያላንተ ፡ ተስፋ ፡ እንደሌለኝ ያላንተ ፡ ተስፋ ፡ እንደሌለኝ (፪x) አንተን ፡ የታመነ ፡ ሰው ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሳይደምር/ሳይጨምር የተረጋገጠ ፡ ነው ፡ ፍጻሜው ፡ እንደሚያምር (፪x) ታድያ ፡ እኔ ፡ ተስፋዬ ፡ ማነው እግዚአብሔር ፡ አይደለም ፡ ዎይ (፪x) አሁንስ ፡ ተስፋዬ ፡ ማነው እግዚአብሔር ፡ አይደለም ፡ ዎይ (፪x) አዋቂው ፡ በዕውቀቱ ፡ አይመካ ጻድቁም ፡ በጽድቁ ፡ አይመካ ፀላይም ፡ በፀሎቱ ፡ አይመካ ጿሚዉም ፡ በመጾሙ ፡ አይመካ ፍርድንና ፡ ጽድቅን ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ የሚያደርግ እርሱ ፡ መሆኑን ፡ በማወቁ ፡ ብቻ በእርሱ ፡ ይመካ (፪x) ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር ንጹህ ፡ ፍፁም ፡ ነውር ፡ የሌለህ (፪x) አንተ ፡ ነውር ፡ የለህም አንተ ፡ እድፈት ፡ የለህም አንተ ፡ ጉድለት ፡ የለህም አንተ ፡ እንከን ፡ የለህም (፪x) አንተ ፡ ራስህ ፡ እውነት ፡ ነህ ምንም ፡ ውሸት ፡ የለብህ ኦ ፡ የለብህ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.