Loading
ትልቅ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ አእምሮ ፡ ሊሸከመው ፡ ከሚችለው ፡ በላይ (፬x) ኦ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ትልቅ (፫x) ኦ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ትልቅ (፫x) እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ትልቅ ፡ ነው (፪x) ትልቅነትህን ፡ ያላየ ፡ ማነው (፫x) ትልቅነትህን ፡ ያልሰማ ፡ ማነው (፫x) እኔስ ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ መብለጥህን እኔ ፡ እንኳን ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን ከነገሮች ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ መብለጥህን እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን ከሁኔታዎች ፡ አንተ ፡ መብለጥህን አንተ ፡ እኮ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪x) አምላኬ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪x) በሠማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ላለኸው ምሥጋናዬ ፡ ይኸው ፣ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው በሠማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ላለኸው አምልኮዬ ፡ ይኸው ፣ አምልኮዬ ፡ ይኸው አይመረመርም ፡ ከፍ ፡ ማለቱ ፡ የእርሱ ፡ ልቀቱ ፡ ጌታዬ አይመረመርም ፡ ተወዳዳሪ ፡ አቻ ፡ ማጣቱ ፡ ጌታዬ አይመረመርም ፡ ውበት ፡ ቁንጅና ፡ ድምቀት ፡ ማማሩ ፡ ጌታይ አይመረመርም ፡ ግርማ ፡ ሞገሱ ፡ አስፈሪነቱ ፡ ጌታዬ ሃ ፡ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፬x) አይመረመርም ፡ የርህራሄው ፡ የምህረቱ ፡ ብዛቱ አይመረመርም ፡ ቸርነቱ ፡ ይቅር ፡ ማለቱ ፡ ጌታዬ አይመረመርም ፡ ፍቅሩ ፡ ጥልቀቱ ፡ ወርዱ ፡ ስፋቱ አይመረመርም ፡ ሰውን ፡ መውደዱ ፡ አዳኝነቱ ፡ ጌታዬ ሃ ፡ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፬x) ትልቅ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ አእምሮ ፡ ሊሸከመው ፡ ከሚችለው ፡ በላይ (፬x) ኦ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ትልቅ (፫x) ኦ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ትልቅ (፫x) እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ትልቅ ፡ ነው (፪x) ትልቅነትህን ፡ ያላየ ፡ አለ ፡ ወይ? (፫x) ትልቅነትህን ፡ ያልሰማ ፡ አለ ፡ ወይ? (፫x) እኔኮ ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ መብለጥህን እኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ትልቅነትህን ከሁኔታዎች ፡ አንተ ፡ መብለጥህን አንተ ፡ እኮ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪x) አምላኬ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪x) የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የምድር ፡ ፈጣሪ በዘለዓለም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነዋሪ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች (፪x) የነገሥታት ፡ ንጉሥ ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች (፪x) የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች (፪x) ነፍሴ ፡ ታከብርሃለች (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.