Loading
በሰማያት ፡ ካለው ፡ ከክብር ፡ ዙፋኔ ክብሬን ፡ ሁሉ ፡ ትቼ ፡ መውረዴ ፡ እኔ አምላክ ፡ ሆኜ ፡ ሳለሁ ፡ ከበረት ፡ ማደሬ ለአንተ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ እንዲህ ፡ መዋረዴ አዝ፦ ተው ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ወደ ፡ ቀድሞው ፡ ስፍራህ እባክህ ፡ አድምጠኝ ፡ ቆሜ ፡ ስጣራ ዓይኔ ፡ እያየችህ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ስትሄድ አንጀቴ ፡ ታወከች ፡ ለእሳት ፡ ስትሟገት ተው ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ወደ ፡ ቀድሞው ፡ ስፍራህ የጭንቄ ፡ ተካፋይ ፡ አጋዥም ፡ ሳይኖረኝ የሞት ፡ ጣርም ፡ ይዞኝ ፡ የደም ፡ ላብ ፡ ሲያልበኝ ይህን ፡ መከራዬን ፡ እንዴት ፡ እረሳኸው ፊትህን ፡ አዙረህ ፡ እኔን ፡ የከዳኸው አዝ፦ ተው ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ወደ ፡ ቀድሞው ፡ ስፍራህ እባክህ ፡ አድምጠኝ ፡ ቆሜ ፡ ስጣራ ዓይኔ ፡ እያየችህ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ስትሄድ አንጀቴ ፡ ታወከች ፡ ለእሳት ፡ ስትሟገት ተው ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ወደ ፡ ቀድሞው ፡ ስፍራህ በጅራፍ ፡ ስገረፍ ፡ ሥጋዬም ፡ ሲቆረስ በጦር ፡ ተወግቼ ፡ ደሜ ፡ እንደውኃ ፡ ሲፈስ የሾህ ፡ አክሊል ፡ ጭኜ ፡ መስቀል ፡ ላይ ፡ መሞቴ እባክህ ፡ ይሰማህ ፡ ይህ ፡ ለማን ፡ ነው ፡ ልጄ አዝ፦ ተው ፡ ተመለስ ፡ ልጄ ፡ ወደ ፡ ቀድሞው ፡ ስፍራህ እባክህ ፡ አድምጠኝ ፡ ቆሜ ፡ ስጣራ ዓይኔ ፡ እያየችህ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ ስትሄድ አንጀቴ ፡ ታወከች ፡ ለእሳት ፡ ስትሟገት
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.