Loading
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ይዘመናቱ ፡ የታሪክ ፡ ጌታ የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የማይረታ (፪x) ብዙ ፡ ብርቱዎች ፡ በምድር ፡ ነበሩ ሊገዳደሩ ፡ ፍፁም ፡ የጣሩ ስራቸው ፡ ሁሉ ፡ እንደጉም ፡ በኗል አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ዛሬም ፡ ከብረሃል አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ይዘመናቱ ፡ የታሪክ ፡ ጌታ የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የማይረታ (፪x) በዘመናት ፡ ውስጥ ፡ የተቋቋመህ ከቶ ፡ ማን ፡ ነበር ፡ አንተን ፡ የረታህ ትጥቅህ ፡ ጠንካራ ፡ ብርቱ ፡ ሰልፈኛ የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ታላቅ ፡ ጦረኛ አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ይዘመናቱ ፡ የታሪክ ፡ ጌታ የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የማይረታ (፪x) በምድር ፡ በሰማይ ፡ ይህ ፡ ሥልጣን ፡ ያለህ ፍጥረታት ፡ ሁሉ ፡ የሚሰግዱልህ ሞገስህ ፡ ትልቅ ፡ ወሰን ፡ የሌለው የእስራኤል ፡ ቅዱስ ፡ ሚመስልህ ፡ ማነው አዝ፦ ምሥጋና ፡ ይሁን ፡ ምሥጋና ምሥጋና ፡ ለእርሱ ፡ ምሥጋና ይዘመናቱ ፡ የታሪክ ፡ ጌታ የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ የማይረታ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.