Loading
እያስገረመኝ ፡ አሃሃሃ ፡ እያስደነቀኝ ፡ አሃሃሃ የአንተ ፡ ምህረት ፡ አሃሃሃ ፡ ቃላት ፡ አሳጣኝ ፡ አሃሃሃ መሽቶ ፡ እስኪነጋ ፡ አሃሃሃ ፡ መቁጠር ፡ እስከሚያቅት ፡ አሃሃሃ የአንተን ፡ ደግነት ፡ አሃሃሃ ፡ እንከን ፡ የሌለበት ፡ አሃሃሃ አዝ፦ ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ወዳጄ ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ይኸውና ፡ በእጄ/ከእጄ ከልቤ ፡ የፈለቀ ፡ የምሥጋና ፡ መስዋዕት እሰዋልሃለሁ ፡ አሽተተው ፡ የእኔ ፡ አባት (፪x) ተፈጸመ ፡ ብሎ ፡ ነግሮኛል ፡ ጌታዬ ፡ አሃሃሃ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ውሎ ፡ አሃሃሃ ፡ ተከፍሎ ፡ እዳዬ ፡ አሃሃሃ እንዲህ ፡ እንዲያ ፡ እያለ ፡ ማነው ፡ የሚከሰኝ ፡ አሃሃሃ ብሩክ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ አሃሃሃ ፡ ጠበቃ ፡ ስላለኝ ፡ አሃሃሃ አዝ፦ ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ወዳጄ ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ይኸውና ፡ በእጄ/ከእጄ ከልቤ ፡ የፈለቀ ፡ የምሥጋና ፡ መስዋዕት እሰዋልሃለሁ ፡ አሽተተው ፡ የእኔ ፡ አባት (፪x) እስቲ ፡ ልነሳና ፡ አሃሃሃ ፡ ወደቤቴ ፡ ልውጣ ፡ አሃሃሃ ለያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ አሃሃሃ ፡ መስዋዕቴን ፡ ልሰዋ ፡ አሃሃሃ እንደ ፡ ስፍሪዳ ፡ አሃሃሃ ፡ ያማረ ፡ ምሥጋና ፡ አሃሃሃ ላምጣ ፡ ልሰዋልህ ፡ አሃሃሃ ፡ ደግ ፡ አምላክ ፡ ነህና ፡ አሃሃሃ አዝ፦ ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ተባረክ ፡ ወዳጄ ምሥጋና ፡ ነው ፡ ያለኝ ፡ ይኸውና ፡ በእጄ/ከእጄ ከልቤ ፡ የፈለቀ ፡ የምሥጋና ፡ መስዋዕት እሰዋልሃለሁ ፡ አሽተተው ፡ የእኔ ፡ አባት (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.