Loading
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ፡ ለምን ፡ ትይኛለሽ የመከራሽን ፡ ቀን ፡ ማነው ፡ ያሳለፈሽ ለአንቺ ፡ የማላስብ ፡ ጨካኝ ፡ አይደለሁም ዝም ፡ ብልሽ ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ አልረሳሽም ለአንቼ ፡ የገባሁትን ፡ የተስፋ ፡ ቃሌን ምነው ፡ በጥቂቱ ፡ ተጠራጠርሺኝ በሃዘን ፡ አልቅሰሽ ፡ ለምን ፡ አስጨነቅሺኝ ስለምንስ ፡ ልጄ ፡ ጌታ ፡ ረሳኝ ፡ አልሺኝ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ፡ ለምን ፡ ትይኛለሽ የመከራሽን ፡ ቀን ፡ ማነው ፡ ያሳለፈሽ ለአንቺ ፡ የማላስብ ፡ ጨካኝ ፡ አይደለሁም ዝም ፡ ብልሽ ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ አልረሳሽም የሚያጽናናኝ ፡ የለም ፡ መንገድ ፡ ዳር ፡ ጥሎኛል እግዚአብሔር ፡ እንደሰው ፡ ፊቱን ፡ ከእኔ ፡ አዙሯል ተለዋዋጭ ፡ አምላክ ፡ እንደሰው ፡ ሆነብኝ ብለሽ ፡ አምተሽኛል ፡ ጌታዬ ፡ እንኳን ፡ ጣለኝ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ፡ ለምን ፡ ትይኛለሽ የመከራሽን ፡ ቀን ፡ ማነው ፡ ያሳለፈሽ ለአንቺ ፡ የማላስብ ፡ ጨካኝ ፡ አይደለሁም ዝም ፡ ብልሽ ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ አልረሳሽም በሃዘን ፡ ቀጠረኝ ፡ በድካም ፡ ከበበኝ ፍርዴን ፡ አጣመመው ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ተወኝ በሙላት ፡ ከቤቴ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ መጣሁኝ ባዶዬን ፡ አስቀረኝ ፡ ስለምንስ ፡ አልሽኝ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ፡ ለምን ፡ ትይኛለሽ የመከራሽን ፡ ቀን ፡ ማነው ፡ ያሳለፈሽ ለአንቺ ፡ የማላስብ ፡ ጨካኝ ፡ አይደለሁም ዝም ፡ ብልሽ ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ አልረሳሽም ጉድጓድ ፡ እንድትገቢ ፡ ጠላት ፡ ከማሰልሽ ከእሳት ፡ አውጥቼሽ ፡ ከመቼው ፡ ተረሳሽ እስቲ ፡ መለሽ ፡ ብለሽ ፡ ባርኮጽህን ፡ ቁተሪ እባክሽን ፡ ልጄ ፡ እንዲህ ፡ አታምርሪ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ፡ ለምን ፡ ትይኛለሽ የመከራሽን ፡ ቀን ፡ ማነው ፡ ያሳለፈሽ ለአንቺ ፡ የማላስብ ፡ ጨካኝ ፡ አይደለሁም ዝም ፡ ብልሽ ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ አልረሳሽም አጭር ፡ ዝምታዬ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ያስመረረሽ ጭር ፡ ያለው ፡ በረሃ ፡ ያጣልኩ ፡ ያስመሰለሽ በክረምቱ ፡ ዝናብ ፡ እረሰርስሻለሁ ያስጨነቀሽንም ፡ ሁሉ ፡ ገስጻለሁ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ትቶኛል ፡ ለምን ፡ ትይኛለሽ የመከራሽን ፡ ቀን ፡ ማነው ፡ ያሳለፈሽ ለአንቺ ፡ የማላስብ ፡ ጨካኝ ፡ አይደለሁም ዝም ፡ ብልሽ ፡ እንኳን ፡ ቢሆን ፡ አልረሳሽም እስቲ ፡ አመስግኒኝ ፡ ማልቀሱን ፡ ተይና ጠላትሽን ፡ በፊቴ ፡ አሳፍሪውና በቤትሽ ፡ በጓዳሽ ፡ ሁሉ ፡ እገባና አነቃሻለሁ ፡ ዳግም ፡ እሰራሽና ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ስላሰብከን ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስላየኸን ተመስገን ፡ ኢየሱስ ፡ ስላሰብከን
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.