Loading
መከራው ፡ በዝቶ ፡ ዛሬማ ፡ ጭንቅ ፡ ሆኖብሃል ሚያዝ ፡ ሚጨበጥ ፡ ከፊትህ ፡ ሁሉ ፡ ርቆሃል ተስፋ ፡ በመቁረጥ ፡ በርህን ፡ ዘግተህ ፡ ተቀምጠህ አበቃ ፡ የእኔማ ፡ ነገር ፡ ብልህ ፡ ደምድመህ ዜናው ፡ ዜናው ፡ ተሰማ የፍቅር ፡ አምላክ ፡ አለና ፡ ወገን ፡ ተጽናና አዝ፦ የመጽናናት ፡ አባት ፡ የርህራሄ ፡ አምላክ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነው ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነው ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው (፪x) ስለዚህ ፡ ወንድሜ ፡ ስለዚህ ፡ ወገኔ ፡ ተጽናና ኢየሱስ ፡ አለና (፬x) ኢየሱስ ፡ አለና (፬x) ተደግፈኸው ፡ አልጣለህ ፡ እርሱን ፡ ተማምነህ ተተግተኸው ፡ አልሸሸህ ፡ ደካማ ፡ ሆነህ ዓይኖቹ ፡ ዛሬም ፡ ያያሉ ፡ ከቶ ፡ አልደከሙም ሰፊ ፡ ትከሻው ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ ይሸከማሉ አይዞህ ፡ አይዞህ ፡ ተጽናና ክብርህን ፡ ጥለህ ፡ አምልከው ፡ ላደረገህ ፡ ቀና አዝ፦ የመጽናናት ፡ አባት ፡ የርህራሄ ፡ አምላክ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነው ከአንቺ ፡ ጋር ፡ ነው ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው (፪x) ስለዚህ ፡ ወንድሜ ፡ ስለዚህ ፡ ወገኔ ፡ ተጽናና ኢየሱስ ፡ አለና (፬x) ኢየሱስ ፡ አለና (፬x) ጌታ ፡ እያለ ፡ የምን ፡ ማዘን ፡ ነው ለእርሱ ፡ አስረክቦ ፡ እርፍ ፡ ማለት ፡ ነው ሃዘኔ ፡ ጠፍቶ ፡ እምባዬ ፡ ታብሷል ሁሉም ፡ አለፈ ፡ አስረስቶኛል አላዝንም ፡ ከእንግዲህ ፡ በቃ ፡ እኔ (፬x) ጌታ ፡ እያለ ፡ ከጐኔ እርሱ ፡ እያለ ፡ ከጐኔ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.