Loading
እጄን ፡ አልሰጥም ፡ ለሚጐትተኝ ፊት ፡ አልሳይም ፡ ለሚሟገተኝ የፊቴን ፡ እያየሁ ፡ እዘረጋለሁ መቆም ፡ አልሻም ፡ በእርሱ ፡ ፈጥናለሁ (፪x) አዝ፦ አልቆምም (፰x) ገና ፡ እሄዳለሁ ፡ በከፍታ ፡ ላይ እገሰግሳለሁ ፡ ኋላዬን ፡ ሳላይ አንዴ ፡ ቀብቶ ፡ ፈቶ ፡ ለቆኛል በእኔ ፡ የጀመረውን ፡ ገና ፡ ይቀጥላል (፪x) አዝ፦ አልቆምም (፰x) ጅምሩ ፡ ገና ፡ ታናሽ ፡ ቢሆንም ጥሶ ፡ ይሄዳል ፡ የሚይዘው ፡ የለም ቃልኪዳን ፡ አለኝ ፡ ከአምላኬ ፡ ጋር እርሱን ፡ አክብሬ ፡ እኔም ፡ ልከብር አዝ፦ አልቆምም (፰x) ታምኜዋለሁ ፡ እንደሚረዳኝ እስከፍጻሜው ፡ እንደሚመራኝ እሄዳለሁኝ ፡ ክንዱን ፡ ታምኜ እወራሳለሁኝ ፡ የበላይ ፡ ሆኜ (፪x) አዝ፦ አልቆምም (፰x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.