Loading
አዝ፦ በእውነት ፡ ለሚወዱህ ፡ እንደሃሳብህ ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ ሁሉ (፰x) መገፋት ፡ መሰደዴ ፡ ወደ ፡ ግብጽም ፡ መውረዴ ወዶኝ ፡ ነው ፡ ያደረገው ፡ አላማ ፡ በእኔ ፡ ስላለው ወጣሁ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ የበላይ ፡ አደረገኝ ተሾምኩኝ ፡ ተመረጥኩኝ ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ሆነልኝ (፪x) ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ሆነልኝ (፬x) አዝ፦ በእውነት ፡ ለሚወዱህ ፡ እንደሃሳብህ ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ ሁሉ (፬x) ሃዘን ፡ ሆነ ፡ መቸገሬ ፡ ኋላ ፡ ግን ፡ ሆነ ፡ ለክብሬ አለፍኩት ፡ እንደዋዛ ፡ መከራዬ ፡ ረግፎ ፡ እንደጤዛ ኑሮዬን ፡ እንዲህ ፡ አጣፍጦ ፡ ዘመርኩኝ ፡ ሁሉ ፡ ተረስቶ ሆነልኝ ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ጌታ ፡ ነገሬን ፡ ውብ ፡ አድርጐ (፪x) ጌታ ፡ ነገሬን ፡ ውብ ፡ አድርጐ (፬x) አዝ፦ በእውነት ፡ ለሚወዱህ ፡ እንደሃሳብህ ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ ሁሉ (፬x) አይበቃም ፡ እዘምራለሁ ፡ ለአምላኬ ፡ እኔ ፡ እቀኛለሁ አምሮልኝ ፡ ሁሉ ፡ ውብ ፡ ሆኗል ፡ መከራዬ ፡ ድልድይ ፡ ሆኖኛል ተሻገርኩ ፡ ሁሉን ፡ አልፌ ፡ አለሁኝ ፡ ከሞት ፡ ተርፌ አይቶልኝ ፡ እዚህ ፡ አድርሶኛል ፡ አክብሮ ፡ ያዘምረኛል (፪x) አክብሮ ፡ ያዘምረኛል (፬x) አዝ፦ በእውነት ፡ ለሚወዱህ ፡ እንደሃሳብህ ፡ ደግሞ ፡ ለተጠሩ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ፡ ሁሉ (፰x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.