Loading
አዝ፦ ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ሁሉ ፡ ሆኖ በዓይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ምስኪኑ ፡ ከብሮ በአንተ ፡ የታደለ ፡ የተመቸው እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ኧረ ፡ ማነው (፪x) ለእኔስ ፡ የደላኝ ፡ የተመቸኝ እፎይ ፡ ያልኩበት ፡ ያሳረፈኝ እንደርሱ ፡ ማነው ፡ የሚደላ የሚመች ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ የሆነኝ ፡ ከለላ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ሁሉ ፡ ሆኖ በዓይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ምስኪኑ ፡ ከብሮ በአንተ ፡ የታደለ ፡ የተመቸው እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ኧረ ፡ ማነው የምመካበት ፡ መመኪያዬ ምታመንበት ፡ መታመኚያዬ የምኮራበት ፡ ጽኑ ፡ ጋሻዬ ኢየሱሴ ፡ ነው ፡ ማረፊያዬ ታድያለሁ ፡ ሆኖኛል ፡ ጥላዬ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ሁሉ ፡ ሆኖ በዓይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ምስኪኑ ፡ ከብሮ በአንተ ፡ የታደለ ፡ የተመቸው እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ኧረ ፡ ማነው ጋሻ ፡ የሆነኝ ፡ ጽኑ ፡ መከታ ጉልበቴ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ እንዳልረታ በአንዳች ፡ አልሰጋም ፡ አልጨነቅም ሥጋቴን ፡ ወስዷል ፡ ሥጋት ፡ አላውቅም እፎይ ፡ ብያለሁ ፡ በመድሃኒያለም አዝ፦ ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ሁሉ ፡ ሆኖ በዓይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ምስኪኑ ፡ ከብሮ በአንተ ፡ የታደለ ፡ የተመቸው እንደ ፡ እኔ ፡ ማነው ፡ ኧረ ፡ ማነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.