Loading
ስለበላሁ ፡ ስለጠጣሁ ፡ አልከተልህም ፡ እኔ ፈቃድህን ፡ እያደረኩ ፡ እኖራለሁ ፡ በዘመኔ (፪x) አይረሳኝ ፡ ትላንት ፡ ያደረገው አስገረመኝ ፡ ለካ ፡ እርሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው አሰናብቶ ፡ ሌላውን ፡ ሲሸኝ ሊሰራብኝ ፡ እኔን ፡ ግድ/ቆይ ፡ አለኝ (፪x) አዝ፦ እኔስ ፡ የቀመስኩት ፡ እኔስ ፡ በዓይኔ ፡ ያየሁት ፡ ነገር ፡ አለ አንተ ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ መርጬሃለሁ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ መርጬሃለሁ (፪x) ጌታ ፡ አንተን ፡ ብዬ ፡ ስምህን ፡ ጠርቼ ነገር ፡ የሞላ ፡ ቀን ፡ ስራህን ፡ ሰርቼ በሆዴ ፡ እንዳልታለል ፡ ሲሞላ ፡ የልቡ ፡ ደርሶ እንዳይሸሽ ፡ ጥሎ ፡ እንዳይሄድ ፡ ባመጣው ፡ እግሩ ፡ ገስግሶ አይሆነው ፡ ያለአንተ ፡ ኑሮ ፡ ልቤ ፡ አውቆሃል ፡ ከአምናው ፡ ዘንድሮ አዝ፦ እኔስ ፡ የቀመስኩት ፡ እኔስ ፡ በዓይኔ ፡ ያየሁት ፡ ነገር ፡ አለ አንተ ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ መርጬሃለሁ (፪x) ወስኜ ፡ ተነሳሁ ፡ ልከተልህ ፡ አንተን ወደ ፡ ኋላ ፡ ትቼው ፡ የራሴን ፡ ነገሬን አንተው ፡ ጋር ፡ ይሻለኛል ፡ ቢሞላም ፡ ቢጐድልም ፡ ሁሉ ከደጅህ ፡ የትም ፡ አልሄድም ፡ እቤትህ ፡ ሁልጊዜ ፡ ሙሉ ደግ ፡ ነህ ፡ እጅህ ፡ ሰፊ ፡ ነው ዘመኔ ፡ ከእግሮችህ ፡ ስር ፡ ነው አዝ፦ እኔስ ፡ የቀመስኩት ፡ እኔስ ፡ በዓይኔ ፡ ያየሁት ፡ ነገር ፡ አለ አንተ ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ መርጬሃለሁ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ መርጬሃለሁ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.