Loading
ዞር ፡ በል ፡ አንተ ፡ ክፉ ፡ ሂድ ፡ ከአጠገቤ ተራዬን ፡ ልጨርስ ፡ ልድረስ ፡ እስከግቤ (፪x) ጌታ ፡ ያየልኝንም ፡ ሄጄ ፡ እስክወርሰው መቆም ፡ አልፈልግም ፡ ልሂድ ፡ ላገልግለው (፪x) አላለቀም ፡ ገና ፡ በእኔ ፡ የጀመረው አላለቀም ፡ ገና ፡ በእኔ ፡ የጀመረው ገለል ፡ በል ፡ ከፊቴ ፡ ጌታን ፡ ላገልግለው ጌታን ፡ ለጌልግለው (፪x) በእኔ ፡ የጀመረውን ፡ ሳይፈጽም ፡ አይቀርም ታማኝ ፡ ነው ፡ በቃሉ ፡ ጌታ ፡ አይረሳኝም እንቅፋት ፡ ልትሆኑ ፡ ገና ፡ ከጅምሩ ቅባቱ ፡ እንዳይወጣ ፡ ይዛቹህ ፡ ልታስሩ አላማዬ ፡ ግቤ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለእኔ አጠገቤ ፡ እትምጡ ፡ ዞርበሉ ፡ ከጐኔ አዝ፦ ገና ፡ ነው ፡ ገና ፡ ገና (፪x) ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላለቀምና ይጨምራል ፡ ገና ገና ፡ ነው ፡ ገና ፡ ገና (፪x) ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላለቀምና ይጨምራል ፡ ገና ይጨምራል ፡ ገና (፬x) ገና ፡ እጓዛለሁ ፡ አምላኬን ፡ ታምኜ አብሬው ፡ ዞራለሁ ፡ ትከሻው ፡ ላይ ፡ ሆኜ ከእንግዲህ ፡ ላትደፍሩ ፡ ሂዱ ፡ ከዚህ ፡ በቃ አምላክ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡ የሁሉም ፡ አለቃ እርሱ ፡ ቀኜን ፡ ይዟል ፡ ፈጽሞ ፡ ላይለቀኝ እከተለዋለሁ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ሚያዋጣኝ አዝ፦ ገና ፡ ነው ፡ ገና ፡ ገና (፪x) ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላለቀምና ይጨምራል ፡ ገና ገና ፡ ነው ፡ ገና ፡ ገና (፪x) ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላለቀምና ይጨምራል ፡ ገና ይጨምራል ፡ ገና (፬x) ብላቴና ፡ እያለሁ ፡ በትንሽነቴ ወንድሞቼን ፡ መርጦ ፡ ረስቶኝ ፡ ሳል ፡ አባቴ አምላኬ ፡ አስጠርቶኝ ፡ ቅባት ፡ ፈሶብኛል ለተለየ ፡ አላማው ፡ እኔን ፡ ፈልጐኛል ስሙን ፡ ማን ፡ ነው ፡ ያሉት ፡ ያ ፡ ያልተገረዘ የእስራኤልን ፡ ልብ ፡ እንዲህ ፡ የበዘበዘ ልሂድ ፡ ልጋጠመው ፡ በአምላኬ ፡ ሥም ፡ ልምታው በላዬ ፡ የፈሰሰው ፡ ሚዘርር ፡ ቅባት ፡ ነው አዝ፦ ገና ፡ ነው ፡ ገና ፡ ገና (፪x) ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላለቀምና ይጨምራል ፡ ገና ገና ፡ ነው ፡ ገና ፡ ገና (፪x) ቅባቱ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አላለቀምና ይጨምራል ፡ ገና ይጨምራል ፡ ገና (፲፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.