Loading
ባለፍኩበት ፡ በሄድኩበት ፡ በመንገዴ ፡ ሁሉ ከነበርኩባቸው ፡ አስጨናቂ ፡ ቀኖቼ ፀጋህ ፡ ምህረትህ ፡ እያገዘኝ ዛሬን ፡ አደረሰኝ አዝ፡ ፡ ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ዛሬን ፡ ለመድረሴ ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ በህይወት ፡ ለመኖሬ (፪x) ከማህፀን ፡ ገና ፡ ሳለሁ ፡ በስሜ ፡ የጠራኸኝ ከልጅነቴ ፡ ጀምሮ ፡ መንገድ ፡ የመራኸኝ ከጥፋት ፡ ጎዳና ፡ ጠበከኝ ፡ ዛሬን ፡ አሳየኸኝ አዝ፡ ፡ ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ዛሬን ፡ ለማየቴ ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ በህይወት ፡ ለመኖሬ (፪x) ከኔ ፡ የሆነ ፡ ከቶ ፡ ምንም ፡ የለም ሁሉ ፡ ባንተ ፡ ነው ፡ የሆነው ከኔ ፡ የሆነ ፡ ከቶ ፡ ምንም ፡ የለም ሁሉ ፡ ካንተ ፡ ነው ፡ የሆነው አዝ፡ ፡ ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ዛሬን ፡ ለመድረሴ ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ በህይወት ፡ ለመኖሬ (፪x) ምክንያቱ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ በህይወት ፡ ለመኖሬ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.