Loading
ያኔ ፡ ገና ፡ በለጋነት ፡ ኑሮ ደርሰህ ፡ ባታወጣኝ ፡ ከጨለማው ፡ ጉዞ እንዴት ፡ እሆን ፡ ነበረ ፡ ያኔ ፡ ለብቻዬ ግን ፡ ሁሉን ፡ አለፍኩት ፡ ካንተ ፡ ጋራ ፡ ሆኜ አይቼሃለሁ ፡ ከጎኔ ፡ ነበርክ ፡ አዝ፡ ፡ አይቼሃለው ፡ ስትረዳኝ ከጎኔ ፡ ሆንህ ፡ ስታግዘኝ ከፊቴ ፡ ሆነህ ፡ ስትመራኝ ስወድቅ ፡ ቀድመህ ፡ ስታነሳኝ (፪x) የቅርብ ፡ ምለው ፡ ካጠገቤ ፡ ርቆ ቀኑ ፡ ጨሎብኝ ፡ ሁኔታውም ፡ ከብዶ አንት ፡ ግን ፡ በሁሉ ፡ ብርታት ፡ ሆነኸኛል እንባዬን ፡ አብሰህ ፡ እጆቼን ፡ ይዘሃል አይቼሃለሁ ፡ ከሆኔ ፡ ነበርክ አዝ፡ ፡ አይቼሃለው ፡ ስትረዳኝ ከጎኔ ፡ ሆንህ ፡ ስታግዘኝ ከፊቴ ፡ ሆነህ ፡ ስትመራኝ ስወድቅ ፡ ቀድመህ ፡ ስታነሳኝ (፪x) አይቼሃለው ፡ አይቼሃለው ፡ አይቼሃለው ፡ ጌታ ስወድቅ ፡ ስታነሳኝ ፡ ከፊት ፡ ስትመራኝ ፡ አይቼሃለው ፡ ጌታ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.