Loading
አዝ፦ ለአንተ ፡ የሚሳንህ ፡ መቼም ፡ የለምና የድንጋይ ፡ ልብን ፡ የሥጋ ፡ አድርግና በምህረት ፡ ዓይንህ ፡ ተመልከተንና ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አላቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ና ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አላቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x) ስለኃጢአቱ ፡ የሞትክለት ፡ ህዝብ በዚህ ፡ ዓለም ፡ ገዚ ፡ ልቡ ፡ ተያዘልህ አንተ ፡ በቀጭኑ ፡ መንገድ ፡ ኑ ፡ ትላለህ ህዝብህ ፡ ግን ፡ በሰፊው ፡ ገብቶ ፡ አለቀልህ መልሰው ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ናለት አዝ፦ ለአንተ ፡ የሚሳንህ ፡ መቼም ፡ የለምና የድንጋይ ፡ ልብን ፡ የሥጋ ፡ አድርግና በምህረት ፡ ዓይንህ ፡ ተመልከተንና ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አላቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x) ክብርህን ፡ በመተው ፡ እራህን ፡ አዋርደህ ሥጋ ፡ በመልበስ ፡ በምድር ፡ ተንከራተህ የሞትክለት ፡ ህዝብህ ፡ ኃይሉ ፡ ትጨፍኗል ማስተዋሉ ፡ ጠፍቶ ፡ ልቡ ፡ ተተብትቧል ጐብኚ ፡ አንተ ፡ ነህና ፡ ኢየሱስ ፡ ጐብኘን ፡ ይላል አዝ፦ ለአንተ ፡ የሚሳንህ ፡ መቼም ፡ የለምና የድንጋይ ፡ ልብን ፡ የሥጋ ፡ አድርግና በምህረት ፡ ዓይንህ ፡ ተመልከተንና ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አላቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x) ለአባቶቻችን ፡ እንደረዳሃቻው ከግብጽ ፡ ባርነት ፡ እንዳወጣሃቸው እንዳወረስካቻው ፡ የተስፋውን ፡ ቦታ እኛም ፡ ከዚህ ፡ ዓለም ፡ ገዢም ፡ ሥር እንፈታ ፡ ጐብኘን ፡ ጌታ አዝ፦ ለአንተ ፡ የሚሳንህ ፡ መቼም ፡ የለምና የድንጋይ ፡ ልብን ፡ የሥጋ ፡ አድርግና በምህረት ፡ ዓይንህ ፡ ተመልከተንና ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አላቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x) ከአንበሶች ፡ ጉድጓድ ፡ የሚያወጣው ፡ ኃይልህ ከእሳት ፡ ነበልባል ፡ የሚያወጣው ፡ ክንድህ ዛሬም ፡ በእኛ ፡ ዘመን ፡ እባክህ ፡ ይዘርጋ ህዝብህን ፡ አድነው ፡ ከሰይጣን ፡ መንጋጋ እኛን ፡ እርዳን ፡ እንድንተጋ አዝ፦ ለአንተ ፡ የሚሳንህ ፡ መቼም ፡ የለምና የድንጋይ ፡ ልብን ፡ የሥጋ ፡ አድርግና በምህረት ፡ ዓይንህ ፡ ተመልከተንና ከዚህ ፡ ዓለም ፡ አላቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቶሎ ፡ ና ማራናታ ፡ ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ና (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.