Loading
አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት እንድ ፡ ሃሳቡም ፡ ለተጠሩ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ ፡ እናውቃለን ስለዚህ ፡ ጌታን (፫x) እናመሰግናለን (፪x) እርሱ ፡ አይሳሳትም ፡ ሁልጊዜ ፡ ልክ ፡ ነው ደግሞም ፡ የሚሆነው ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው የእኛ ፡ ሃሳብ ፡ ካልሆነ ፡ ይቅር ፡ ምሬታችን የያዝነውን ፡ ጌታ ፡ መጠራጠራችን (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት እንድ ፡ ሃሳቡም ፡ ለተጠሩ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ ፡ እናውቃለን ስለዚህ ፡ ጌታን (፫x) እናመሰግናለን የፀሎት ፡ መልስ ፡ ቢዘገይ ፡ ቢሆንም ፡ ዝምታ ብዙ ፡ ጥያቄዬ ፡ እንኳን ፡ መልስ ፡ ቢያጣ የጠራኝ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እኔስ ፡ አምነዋለሁ ስንቱን ፡ አሳልፎኝ ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት እንድ ፡ ሃሳቡም ፡ ለተጠሩ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ ፡ እናውቃለን ስለዚህ ፡ ጌታን (፫x) እናመሰግናለን በለሱን ፡ የጠበቀ ፡ ፍሬዋን ፡ ይበላል ጌታውን ፡ የሚጠብቅ ፡ ደግሞ ፡ ይከብራል ብዙ ፡ አድርጐልኛል ፡ እመሰክራለሁ እናንተም ፡ እመኑት ፡ ደግሜ ፡ እላለሁ (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት እንድ ፡ ሃሳቡም ፡ ለተጠሩት ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ ፡ እናውቃለን ስለዚህ ፡ ጌታን (፫x) እናመሰግናለን የሚያልፍ ፡ ባይመስልም ፡ በዝቶ ፡ ችግራችን የራቀ ፡ ቢመስልም ፡ጌታ፡ ከጐናችን ቆመን ፡ እንጠብቀው ፡ በመጠበቂያችን ተስፋውን ፡ የሰጠን ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታችን (፪x) አዝ፦ እግዚአብሔርን ፡ ለሚወዱት እንድ ፡ ሃሳቡም ፡ ለተጠሩት ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ እንዲደረግ ፡ እናውቃለን ስለዚህ ፡ ጌታን (፫x) እናመሰግናለን
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.