Loading
አዝ፦ ልበል ፡ እንደ ፡ ማርያም ፡ ሚላችሁን ፡ አርጉ እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ አንዳች ፡ እንዳትሰጉ አንድ ፡ ነገር ፡ ብቻ ፡ አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ ገብቶኛል ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ካለ ፡ እሰይ ፡ ይበቃኛል (፪x) ሰዎች ፡ ሰርግ ፡ ደግሰው ፡ እጅግ ፡ በሰፊው የወይን ፡ ጠጁ ፡ አልቆ ፡ ጉድ ፡ አረጋቸው ሲወጡ ፡ ሲገቡ ፡ ተጨንቀው ፡ እያለ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ አሃሃ ፡ ለካስ ፡ እዚያ ፡ ቤት ፡ አለ ኢየሱስ ፡ ጣልቃ ፡ ገባ ፡ ዲያብሎስ ፡ ከሰረ ውሃው ፡ ግሩም ፡ ጣዕም ፡ ያለው ፡ ወይን ፡ ጠጅ ፡ ሆነ አዝ፦ ልበል ፡ እንደ ፡ ማርያም ፡ ሚላችሁን ፡ አርጉ እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ አሜን ፡ አንዳች ፡ እንዳትሰጉ አንድ ፡ ነገር ፡ ብቻ ፡ አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ ገብቶኛል ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ካለ ፡ አሜን ፡ ይበቃኛል ወገኖች ፡ እኛንም ፡ ችግር ፡ ሲገጥመን እንበለው ፡ እንደዚህ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስን ኢየሱሴ ፡ ግባ ፡ በቤቴ ፡ ታደም ኑሮዬ ፡ ያለአንተ ፡ አሃሃ ፡ ትርጉም ፡ የለውም ብቻ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ እርሱ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ደልዳላ ፡ ይሆናል ፡ ትልቁ ፡ ተራራ አዝ፦ ልበል ፡ እንደ ፡ ማርያም ፡ ሚላችሁን ፡ አርጉ እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ አሜን ፡ አንዳች ፡ እንዳትሰጉ አንድ ፡ ነገር ፡ ብቻ ፡ አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ ገብቶኛል ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ካለ ፡ አሜን ፡ ይበቃኛል የኢየሱስ ፡ ወዳጅ ፡ ድንገት ፡ ታመመና ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ ላኩ ፡ ብለው ፡ በቶሎ ፡ ና ጌታም ፡ አልፈጠነ ፡ አሃሃ ፡ አለአዛርም ፡ ሞተ አራት ፡ ቀን ፡ ሆነው ፡ ተቀብሮ ፡ ሸተተ ቢዘገይም ፡ እንኳን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መጣ የሞተው ፡ ከቀብሩ ፡ ሕያው ፡ ሆኖ ፡ ወጣ አዝ፦ ልበል ፡ እንደ ፡ ማርያም ፡ ሚላችሁን ፡ አርጉ እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ አሜን ፡ አንዳች ፡ እንዳትሰጉ አንድ ፡ ነገር ፡ ብቻ ፡ አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ ገብቶኛል ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ካለ ፡ ይሁን ፡ ይበቃኛል ዝናቡ ፡ ፀሃዯ ፡ ነፋሱ ፡ አየሩ እንዳስፈለጋችሁ ፡ ብትቀያየሩ ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው ፡ ምንድን ፡ ያስፈራኛል ቁራን ፡ እየላከ ፡ ቢያስፈልግ ፡ ጮማን ፡ ያበላኛል ስደክም ፡ ኃይል ፡ ሰጥቶ ፡ ስወደቅ ፡ አንስቶ ቤቱ ፡ ያደርሰኛል ፡ ሃያል ፡ ክንዱ ፡ መርቶ አዝ፦ ልበል ፡ እንደ ፡ ማርያም ፡ ሚላችሁን ፡ አርጉ እርሱ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ አሜን ፡ አንዳች ፡ እንዳትሰጉ አንድ ፡ ነገር ፡ ብቻ ፡ አሃሃ ፡ አውቃለሁ ፡ ገብቶኛል ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ካለ ፡ እሰይ ፡ ይበቃኛል (፫x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.