Loading
አዝ፦ ስዝል ፡ ሲያቅተኝ ፡ ስደክም ጌታዬ ፡ አንተ ፡ አልተውከኝም ድምፅህ ፡ መጣ ፡ ለሕይወቴ በረታ ፡ ቁርጭምጭሚቴ ፡ ክበር ፡ መድሃኒቴ (፪x) ልባችን ፡ ሲዝል ፡ ሲደነድን አለህ ፡ ማድቀቁያ ፡ መዶሻ ፡ ቃል ለደረቀ ፡ አጥንት ፡ ሕይወት ፡ ይሰጣል ታላቅ ፡ ሰራዊት ፡ አርጐ ፡ ያቆማል አዝ፦ ስዝል ፡ ሲያቅተኝ ፡ ስደክም ጌታዬ ፡ አንተ ፡ አልተውከኝም ድምጽህ ፡ መጣ ፡ ለሕይወቴ በረታ ፡ ቁርጭምጭሚቴ ፡ ክበር ፡ መድሃኒቴ ዛፍ ፡ ስር ፡ ስንወድቅ ፡ አይሎ ፡ ሰልፍ የስንፍናን ፡ ቃል ፡ ስንለፈልፍ ትከሻህ ፡ አይዝል ፡ ፊትህ ፡ አይጠቁርም የወደድከውን ፡ ሰውን ፡ አትጥልም አዝ፦ ስዝል ፡ ሲያቅተኝ ፡ ስደክም ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ አልተውከኝም ቃልህ ፡ መጣ ፡ ለሕይወቴ በረታ ፡ ቁርጭምጭሚቴ ፡ ክበር ፡ መድሃኒቴ ቃልህ ፡ ጅማትን ፡ ቅልጥም ፡ ይወጋል ነፍስንና ፡ መንፈስንም ፡ ይለያል በምክሩም ፡ ግሩም ፡ ጣፋች ፡ ሲበላ እንከን ፡ የሌለው ፡ የማር ፡ ወለላ አዝ፦ ስዝል ፡ ሲያቅተኝ ፡ ስደክም ጌታያ ፡ አንተ ፡ አልተውከኝም ድምጽህ ፡ መጣ ፡ ለሕይወቴ በረታ ፡ ቁርጭምጭሚቴ ፡ ክበር ፡ መድሃኒቴ ኢየሱስ ፡ በቃሉ ፡ የፈወሳችሁ በቅዱስ ፡ መንፈሱ ፡ የነካካችሁ እንደኔ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ደስ ፡ ያላችሁ አክብሩት ፡ ጌታን ፡ እልል ፡ ብላችሁ አዝ፦ ስዝል ፡ ሲያቅተኝ ፡ ስደክም ጌታዬ ፡ አንተ ፡ አልተውከኝም ድምጽህ ፡ መጣ ፡ ለሕይወቴ በረታ ፡ ቁርጭምጭሚቴ ፡ ክበር ፡ መድሃኒቴ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.