Loading
አዝ፦ ኦ ፡ ሃገሬን ፡ አስባት ፡ ኢትዮጵያን ፡ አስባት የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ከፍተህ ፡ ጌታ/ኢየሱስ ሰላም ፡ ለአንቺ ፡ ይሁን ፡ በላት (፪x) እግዚአብሔር ፡ አስባት ፡ ጐብኛት ፡ ኢትዮጵያን እማጸንሃለሁ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አፍስሼ ፡ እንባዬን እግዜአብሄር ፡ ነህ ፡ ለኛ ፡ መድህኒታችን ስለ ፡ ሥምህ ፡ አስብ ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ የተስፋ ፡ ቃልህን አዝ፦ ኦ ፡ ሃገሬን ፡ አስባት ፡ ኢትዮጵያን ፡ አስባት የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ከፍተህ ፡ ጌታ ሰላም ፡ ለአንቺ ፡ ይሁን ፡ በላት (፪x) ለልጅ ፡ ልጅ ፡ የሚተርፍ ፡ ቢኖር ፡ የአባት ፡ በደል መሃሪ ፡ ነህና ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ ይቅር ፡ በል መቅሰፍት ፡ ጉስቁልና ፡ ከእንግዲህስ ፡ ያብቃ ከዙፋንህ ፡ ተነስ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንተ ፡ ግባ ፡ ጣልቃ አዝ፦ ኦ ፡ ሃገሬን ፡ አስባት ፡ ኢትዮጵያን ፡ አስባት የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ከፍተህ ፡ ኢየሱስ ሰላም ፡ ለአንቺ ፡ ይሁን ፡ በላት እጁዋን ፡ አንስታለች ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ከፍ ፡ አድርጋ መፍትሄ ፡ ሚገኘው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ነውና ፡ ከአንተ ፡ ጋ ወንዶችና ፡ ሴቶች ፡ ትልቅ ፡ ትንሾችም እንለምንሃለን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ወድቀን ፡ በእግርህ ፡ ታች አዝ፦ ኦ ፡ ሃገሬን ፡ አስባት ፡ ኢትዮጵያን ፡ አስባት የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ከፍተህ ፡ ጌታ ሰላም ፡ ለአንቺ ፡ ይሁን ፡ በላት ለምድራችን ፡ ከአንተ ፡ ፍቅር ፡ ሰላም ፡ ይምጣ በዲያቢሎስም ፡ ላይ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተነሳ ፡ በቁጣ ሰማይ ፡ ይከፈት ፡ በረከትህ ፡ ይምጣ የተጠማው ፡ ህዝብህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጠጥቶ ፡ እንዲረካ አዝ፦ ኦ ፡ ሃገሬን ፡ አስባት ፡ ኢትዮጵያን ፡ አስባት የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ ከፍተህ ፡ ጌታ/ኢየሱስ ሰላም ፡ ለአንቺ ፡ ይሁን ፡ በላት (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.