Loading
አመታቶችህ ፡ ከቶ ፡ አያልቁም የዘመንህ ፡ ቁጥር ፡ አይመረመርም አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ንጉስ ፡ ነህ ፡ ለእኛ አዝ:- ዙፋንህ ፡ የዘላለም ፡ ነው መንግሥትህ ፡ ማንም ፡ አይሽረው አንተ ፡ ግን ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ዘላለም ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (፪x) ስልጣን ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ መንግስት ፡ የአንተ ፡ ነው አምላክና ፡ አባት ፡ አዳኝ ፡ የሆንከው የሲኦልን ፡ ቁልፍ ፡ በእጅህ ፡ ይዘሃል ጻድቅ ፡ ፈራጅ ፡ ነህ ፡ ክብር ፡ ይገባሃል አዝ:- ዙፋንህ ፡ የዘላለም ፡ ነው መንግሥትህ ፡ ማንም ፡ አይሽረው አንተ ፡ ግን ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ዘላለም ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (፪x) ከጥንት ፡ ጀምሮ ፡ ምድርን ፡ መሰረትክ በእጆች ፡ ሥራ ፡ ሰማይን ፡ ሰራህ የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ አምላክ ፡ አንተ ፡ ነህ ሁሉም ፡ ያልፋሉ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ያው ፡ ነው አዝ:-ዙፋንህ ፡ የዘላለም ፡ ነው መንግሥትህ ፡ ማንም ፡ አይሽረው አንተ ፡ ግን ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ዘላለም ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (፪x) ከስሞች ፡ በላይ ፡ ታላቅ ፡ ስም ፡ ይዘህ በአባትህ ፡ ቀኝ ፡ በክብር ፡ ያለህ የሁሉ ፡ ጌታ ፡ የሁሉ ፡ ንጉስ የእኛም ፡ መድሃኒት ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ አዝ:- ዙፋንህ ፡ የዘላለም ፡ ነው መንግሥትህ ፡ ማንም ፡ አይሽረው አንተ ፡ ግን ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ዘላለም ኢየሱስ ፡ የሚመስልህ ፡ የለም (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.