Loading
አዝ:- ለእኔስ ፡ ከአንተ ፡ ሚበልጥ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝም ፍቅርህ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ ፡ ነው በልቤ ፡ ከቶ ፡ አይበርድም (፪x) በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በልቤ ፡ የፈሰሰው አቤቱ ፡ ፍቅርህ ፡ መተኪያ ፡ የለው (፪x) ብዙ ፡ ውሆች ፡ እንኩዋን ፡ ሊያጠፉት ፡ አልቻሉም ግሩም ፡ ነው ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ፍቅርህ ፡ አይነገርም አዝ:- ለእኔስ ፡ ከአንተ ፡ ሚበልጥ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝም ፍቅርህ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ ፡ ነው በልቤ ፡ ከቶ ፡ አይበርድም (፪x) የብርሃን ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ መመኪያ ፍቅርህ ፡ ሁሌ ፡ አዲስ ፡ ነው ፡ ከልቤ ፡ ማይጠፋ (፪x) አንተን ፡ አንተን ፡ እንጂ ፡ ማንንም ፡ አልልም አምላኬ ፡ ጌታዬ ፡ እኔስ ፡ አልጠግብህም አዝ:- ለእኔስ ፡ ከአንተ ፡ ሚበልጥ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝም ፍቅርህ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ ፡ ነው በልቤ ፡ ከቶ ፡ አይበርድም (፪x) የነፍሴ ፡ ጥጋብ ፡ የሕይወቴ ፡ አለኝታ መጠጊያዬ ፡ ነህ ፡ ብሩኩ ፡ ጌታ (፪x) ነፍሴን ፡ በምሕረትህ ፡ አድነሃልና የመድህንቴ ፡ አምላክ ፡ ይድረስህ ፡ ምስጋና አዝ:- ለእኔስ ፡ ከአንተ ፡ ሚበልጥ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝም ፍቅርህ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ ፡ ነው በልቤ ፡ ከቶ ፡ አይበርድም (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.