Loading
ፅድቅና ፡ መንግሥትህ ፡ እንደምን ፡ ያምራሉ ከአንተ ፡ ወድያ ፡ ሕይወት ፡ ለምን ፡ ያሰኛሉ የአባትነትህ ፡ ፍቅርህ ፡ በኢየሱስ ፡ ያየነው ማርኮ ፡ አስቀርቶናል ፡ ኑሮዋችን ፡ የአንተ ፡ ነው (፪x) አዝ:- ክቡርና ፡ ቅዱስ ፡ ኃያል ልዑል ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር ከአንተ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም አልነበረም ፡ ደግሞ ፡ አይኖርም (፪x) ሥራህን ፡ እያየን ፡ እናደንቅሀለን ሁልጊዜ ፡ ፍቅርህን ፡ ጌታ ፡ እናስባለን መንፈስና ፡ ሥጋ ፡ ነፍሳችን ፡ ተስማምተው ያመሰግኑሃል ፡ ክበር ፡ ጌታ ፡ ብለው (፪x) አዝ:- ክቡርና ፡ ቅዱስ ፡ ኃያል ልዑል ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር ከአንተ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም አልነበረም ፡ ደግሞ ፡ አይኖርም (፪x) ውለታህ ፡ አለብን ፡ ከልብ ፡ የማይጠፋ እኛን ፡ የረዳኸን ፡ ኢየሱስ ፡ ክብርህ ፡ ይስፋ ከቶ ፡ ምን ፡ አለና ፡ ለእኛ ፡ ያላደረከው መድኃኒታችን ፡ ሆይ ፡ ክብራችን ፡ ከአንተ ፡ ነው (፪x) አዝ:- ክቡርና ፡ ቅዱስ ፡ ኃያል ልዑል ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር ከአንተ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም አልነበረም ፡ ደግሞ ፡ አይኖርም (፪x) ከፀሐይ ፡ ሰባት ፡ እጅ ፡ ድምቀህ ፡ ትታያለህ ሁለንተናህ ፡ ውብ ፡ ነው ፡ ምንም ፡ አልጐደለህ ለግርማዊነትህ ፡ ክብር ፡ እንሰግዳለን ልዑል ፡ ሆይ ፡ ለሥምህ ፡ እንዘምራለን (፪x) አዝ:- ክቡርና ፡ ቅዱስ ፡ ኃያል ልዑል ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር ከአንተ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም አልነበረም ፡ ደግሞ ፡ አይኖርም (፬x) ከአንተ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም አልነበረም ፡ ደግሞ ፡ አይኖርም (፪x) አዝ:- ክቡርና ፡ ቅዱስ ፡ ኃያል ልዑል ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር ከአንተ ፡ በቀር ፡ ማንም ፡ የለም አልነበረም ፡ ደግሞ ፡ አይኖርም (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.