Loading
በኃጥያት ፡ ባርነት ፡ ከታሰርንበት የሞትን ፡ ሽታ ፡ ካጣጣምንበት ወደ ፡ ፅድቅ ፡ አደባባይ ፡ ጠርተኸን በሕይወት ፡ መዓዛ ፡ ይኸው ፡ ታወድን የጥሪህ ፡ ተስፋ ፡ አስደናቂ ፡ ነው የርስትህም ፡ ክብር ፡ እኩያ ፡ የለው ስለሰጠኸን ፡ የመዳን ፡ ዕውቀት ተመካን ፡ በኃይልህ ፡ ታላቅነት አማኑኤል (፮x) አሜን ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና (፫x) አስተማማኝ ፡ ነህ ፡ ዘላቂ ፡ ዋስትና ከድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ውስጥ ፡ ወጥተና ከሞት ፡ ጥላም ፡ ሃገር ፡ አምልጠናል በሚደነቅ ፡ ብርሃን ፡ ልታኖረን አዲስ ፡ ምዕራፍ ፡ ተከፈተልን በቃል ፡ ኪዳንህ ፡ እየደገፍከን በሸለቆ ፡ ህግህን ፡ አስተማርከን እስከ ፡ ዘንድሮ ፡ በአንተ ፡ ዘልቀናል ከእጆችህ ፡ መዳፍ ፡ ማን ፡ ያወጣናል አማኑኤል (፮x) አሜን ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና (፫x) አስተማማኝ ፡ ነህ ፡ ዘላቂ ፡ ዋስትና ማግኘት ፡ ማጣት ፡ መብዛት ፡ መጉደልን መክበር ፡ መዋረድ ፡ መራብ ፡ መጥገብን መነቀፍ ፡ መሞገሥም ፡ አይተናል ጉልበት ፡ ሆነኸን ፡ ሁሉን ፡ ችለናል ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ነህ ፡ ማን ፡ ይከሰናል አፀደከን ፡ ማን ፡ ይኮንነናል ከአሸናፊዎች ፡ በአንተ ፡ እንበልጣለን የለም ፡ ከፍቅርህ ፡ የሚነጥለን እንዲህ ፡ መተናል ፡ ያለፈውን ፡ ዘመን ስለ ፡ ነገውስ ፡ ምን ፡ አስጨነቀን ኃያልነትህ ፡ እጅግ ፡ አስመካን ኦ ፡ የእኛ ፡ ጌታ ፡ ተመሥገንልን ዝማሬ ፡ አለን ፡ እስከዛሬ ዕልልታ ፡ ዘላቂ ፡ አለኝታ ጭብጨባ ፡ ሽብሸባ የዘለዓለም ፡ አምባ እኛስ ፡ በጐነት ፡ የለንም
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.