Loading
ተሳዳጅ ፡ እፎይ ፡ ሲል ፡ አሳዳጅ ፡ ሬሳበሬሳ እግዚአብሔር ፡ ክንዱን ፡ ሲያነሳ ጭንቅ ፡ ውስጥ ፡ አገባቸው ፡ አሳያቸው ፡ ፍዳ ፡ አበሳ አንሸሽም ፡ ቢሉ ፡ የማይሆን ፡ ሆነ ፡ ነገሩ ሠራዊቱ ፡ ታወከ ፡ መንከራኩሮቹ ፡ ታሰሩ ባሕሩ ፡ ከደናቸው ፡ ደግሞ ፡ ሳይተያዩ እስራኤል ፡ ተሻገረ ፡ ለዘለዓለም ፡ ተለያዩ[1] አዝ፦ ነገሩ ፡ ተገለበጠ እግዚአብሔር ፡ ሕዝቡን ፡ አስመለጠ ነገሩ ፡ ተገለበጠ አዋጅ ፡ በአዋጅ ፡ ተሻረ ሞት ፡ በሕይወት ፡ ተቀየረ እግዚአብሔር ፡ ተነሳ ፡ ንጉሡን ፡ እንቅልፍ ፡ ነሳው የተዘጋን ፡ መዝገብ ፡ እንዲያገላብጥ ፡ አደረገው መታሰብ ፡ ሆነና ፡ ሃዘን ፡ በደስታ ፡ ተተካ ሁኔታው ፡ ሲለወጥ ፡ ሰቃይ ፡ ተሰቃይ ፡ ነው ፡ ለካ ዋይታና ፡ ስቃይ ፡ ጭንቀት ፡ ሃፍረት ፡ ለጠላታቸው በአይሁድ ፡ የተድላና ፡ የደስታ ፡ ቀን ፡ ሆነላቸው[2] አዝ፦ ነገሩ ፡ ተገለበጠ እግዚአብሔር ፡ ሕዝቡን ፡ አስመለጠ ነገሩ ፡ ተገለበጠ አዋጅ ፡ በአዋጅ ፡ ተሻረ ሞት ፡ በሕይወት ፡ ተቀየረ ከአምላካቸው ፡ በቀር ፡ ቅዱሳን ፡ ስግደት ፡ አያውቁም ሚቆጣ ፡ ቢቀጣ ፡ ጣዖትን ፡ ከቶ ፡ አያመልኩም ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ቢነድ ፡ እቶኑ ፡ ቢብስበትም ያድናል ፡ እርሱ ፡ አንሰግድም ፡ ባያድነንም የጣሏቸው ፡ ሰዎች ፡ ወሳፈን ፡ ገደላቸው የልዑል ፡ አምላክ ፡ ባሮች ፡ ክብር ፡ ተጨመረላቸው[3] አዝ፦ ነገሩ ፡ ተገለበጠ እግዚአብሔር ፡ ሕዝቡን ፡ አስመለጠ ነገሩ ፡ ተገለበጠ አዋጅ ፡ በአዋጅ ፡ ተሻረ ሞት ፡ በሕይወት ፡ ተቀየረ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.