Loading
ምህረቱ ፡ እንደ ፡ ደመና (፪x) ፡ ከቦኛል ልዘምር ፡ የአምላኬን ፡ ምሥጋና (፪x) የዘወትር ፡ ትዝታው ፡ ማስታወሻው እኔን ፡ ባየኝ ፡ ቁጥር ፡ ትዝ ፡ የሚለው የሕይወት ፡ እስትንፋስ ፡ የሆነልኝ ከምህረቱ ፡ በቀር ፡ ምንም ፡ የለኝ ጽድቄ ፡ ቅድስናዬ ፡ ቤዛነቴም ፡ ኢየሱስ ፡ ነው የመዳን ፡ ልብሴ ፡ መጐናጸፊያዬም ፡ እርሱ ፡ ነው ትልቅ ፡ ልግስናው ፡ ቸርነቱ ብቃት ፡ ሆኖ ፡ ያቆመኝ ፡ በፊቱ የማንነቴ ፡ ምንጭ ፡ መገኛዬ ይቅርታው ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የጌታዬ ነፍሱን ፡ ሰጥቶ ፡ ነፍሴን ፡ የተቤዛት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በደሙ ፡ አጥቦ ፡ አዲስ ፡ ንፁህ ፡ ያደረጋት ፡ እርሱ ፡ ነው የረከሰ ፡ ማንነቴን ፡ ሽሮ አደፋውን ፡ ታሪኬን ፡ ቀይሮ በወይኑ ፡ ግንድ ፡ ላይ ፡ የተከለኝ በአደባባዮቹም ፡ ያበቀለኝ አክሊል ፡ እንደለበሰ ፡ ሙሽራ ፡ ያስዋበኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ሞገስ ፡ ደም ፡ ግባት ፡ ዝርግፍ ፡ ጌጥ ፡ የሆነኝ ፡ እርሱ ፡ ነው በምህረቱ ፡ ልጁ ፡ ሆኛለሁ በምህረቱ ፡ ቤቱ ፡ ኖራለሁ በምህረቱ ፡ አመልከዋለሁ በምህረቱ ፡ አገለግላለሁ ምህረቱ ፡ ሕይወቴ ፡ ምህረቱ ፡ ጉልበቴ ምህረቱ ፡ ብቃቴ ፡ ምህረቱ ፡ ትምክህቴ ምህረቱ ፡ እረፍቴ ፡ ምህረቱ ፡ ምችቴ ምህረቱ ፡ ተድላዬ ፡ ምህረቱ ፡ ጥላዬ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.