Loading
ሃብቴ ፡ ነው ፡ ሃብቴ ፡ ሃኪሜም ፡ መድኃኒቴ ከሞት ፡ ጉዞ ፡ መለሰኝ ፡ በሕይወት ፡ ጐዳና ፡ መራኝ ዝናብ ፡ ምድርን ፡ እንዲያርስ ፡ ውስጤን ፡ አረስርሶታል ለአምላኬ ፡ ክብር ፡ እንድኖር ፡ ለፅድቅ ፡ አነቃቅቶኛል የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ይባረክ (፬x) . (1) . ፡ አስደነቀኝ ፡ ፈተሸኝ ፡ መረመረኝ ከክፉ ፡ . (2) . ፡ መክሮ ፡ በልቤ ፡ ተሰውሮ ማስተዋሌን ፡ አስፈትቶ ፡ በትዕዛዙ ፡ ሮጣለሁ የእለት ፡ መመሪያዬ ፡ አስተዳዳሪዬም ፡ ነው የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ይባረክ (፬x) ከመጻሐፍት ፡ በኩር ፡ ታላቅ ፡ መጽሐፍት የማይለወጥ ፡ የማይሻር መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ የአምላኬ ፡ ቃል (፪x) ከሐዘን ፡ መጽናኛዬ ፡ ቀን ፡ ሙሉ ፡ ትዝታዬ ሆኖኝ ፡ ወድጄዋለሁ ፡ ዘወትር ፡ አጫዋቼ ፡ ነው ስስት ፡ ይገስፀኛል ፡ ስዝል ፡ ያበረታኛል ከስንቁ ፡ በልጦብኛል ፡ ነፍሴን ፡ ሕያው ፡ አድርጓታል ለእግሬ ፡ ምብራት ፡ ነው ለመንገዴም ፡ ብርሃን ፡ ነው ከየት ፡ እንደተገኘሁ ፡ ለምን ፡ በምድር ፡ እንዳለሁ በኋላም ፡ መድረሻዬን ፡ አሳየኝ ፡ ገልጦ ፡ ዓይኔን ቁም ፡ ነገረኛ ፡ አድርጐ ፡ ውብ ፡ ዓላማ ፡ አስጨበጠኝ እንደ ፡ ሌላ ፡ ለውጦ ፡ ከሰውም ፡ ሰው ፡ አረገኝ የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ይባረክ (፬x) ከመጻሐፍት ፡ በኩር ፡ ታላቅ ፡ መጽሐፍት የማይለወጥ ፡ የማይሻር መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ የአምላኬ ፡ ቃል (፪x) እንዱ ፡ ከድኖ ፡ ሲስመው ፡ ሌላው ፡ ሲንተራስበት አንዱ ፡ ተረት ፡ ሲመስለው ፡ ሌላው ፡ ሲያላግጥ ለእኔ ፡ ግን ፡ ሆኖኛል ፡ የማይዘለቅ ፡ በረከት (፪x) ብሰማው ፡ ብሰማው ፡ ማዳምጠው ፡ ማዳምጠው ሁሌ ፡ አዲስ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ አዲስ ፡ ነው ባነበው ፡ ባነበው ፡ ባጠናው ፡ ባጠናው የእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ይባረክ (፬x) ከመጻሐፍት ፡ በኩር ፡ ታላቅ ፡ መጽሐፍት የማይለወጥ ፡ የማይሻር መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ የአምላኬ ፡ ቃል (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.