Loading
ይሁን ፡ በሚል ፡ ቃልህ ፡ ብቻ ፡ ሰማያት ፡ ፀኑ ይሁን ፡ በሚል ፡ ቃልህ ፡ ብቻ ፡ ይኸው ፡ ዓለሙ አይተን ፡ የማንጨርሰውን ፡ በእድሜ ፡ ልካችን ይሁን ፡ ይሁን ፡ ብለህ ፡ ብቻ ፡ አበጀኸልን (፪x) የስልጣንህ ፡ ቃል ፡ ካፍህ ፡ ሲወጣ ያልነበረው ፡ ወደ ፡ መኖር ፡ መጣ ታዘዘ ፡ ሁሉም ፡ ብብልሃትህ አንተ ፡ እንዳሰብከው ፡ እንዳየህለት (፪x) ምንጩ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ መገኛ ስኖርም ፡ በአንተ ፡ የአንተ ፡ ጥገኛ ትንፋሼን ፡ እንኳን ፡ ከአንተ ፡ ተውሼ እንዳከብርበት ፡ አንተን ፡ መልሼ እኔ ፡ አላውቀውም ፡ የፀጉሬን ፡ ቁጥር አንተ ፡ ግን ፡ ቆጥረዋለህ እኔ ፡ አላውቀውም ፡ የዘመኔን ፡ ልክ አንተ ፡ ለክተኸዋል እኔማ ፡ በእኔ ፡ አልመጣሁም እኔን ፡ እኔ ፡ አልመራውም እኔነቴን ፡ እኔ ፡ አልወሰንኩም እኔ ፡ የእኔ ፡ አይደለሁም (፪x) መረጥክለኝ ፡ ትውልድ ፡ ሀገሬን መረጥክለኝ ፡ ዘሬን ፡ ጐሳዬን መረጥክልኝ ፡ እናት ፡ አባቴን መረጥክልኝ ፡ መልኬን ፡ ፆታዬን ይሁና ፡ አንተ ፡ ያሰብክልኝ ይሁና ፡ የወደደክልኝ ይሁና ፡ የመረጥክልኝ ይሁን ፡ አሜን ፡ ይሁንልኝ (፪x) አዝ፦ የህይወቴ ፡ ጌታዋ የህይወቴ ፡ ተጠሪዋ የህይወቴ ፡ ባለቤት እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ በእውነት (፪x) ስራ ፡ ሰሪውን ፡ ለምን ፡ እንደዚህ ፡ አረከኝ ፡ እንደማይለው እኔም ፡ ፍጡር ፡ ነኝ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ የወደደውን ፡ ሚያደርገው ሸክላ ፡ ሰሪውን ፡ ለምን ፡ እንደዚህ ፡ አረከኝ ፡ እንደማይለው እኔም ፡ ፍጡር ፡ ነኝ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ የወደደውን ፡ ሚያደርገው ስራ ፡ ሰሪውን ፡ ለምን ፡ እንደዚህ ፡ አረከኝ ፡ እንደማይለው እኔም ፡ ፍጡር ፡ ነኝ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ በእኔ ፡ የወደደውን ፡ የሚያደርገው ሸክላ ፡ ሰሪውን ፡ ለምን ፡ እንደዚህ ፡ መልሰኝ ፡ ቀልሰኝ ፡ አይለውም ስልጣን ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ እንደወደደ ፡ እንደፈቃዱ ፡ ሊያደርገው ቢበላሽም ፡ አፍርሶ ፡ እንደገና ይሰራዋል ፡ ባለቤት ፡ ነዋ ሸክላ ፡ ሰሪው ፡ ሸክላው ፡ በእጁ ፡ እንዳለ የእኔም ፡ ህይወት ፡ በእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ ዋለ (፪x) አዝ፦ የህይወቴ ፡ ጌታዋ የህይወቴ ፡ ተጠሪዋ የህይወቴ ፡ ባለቤት እግዚሀብሄር ፡ ነው ፡ በእውነት (፪x) እኔማ ፡ በእኔ ፡ አልመጣሁም እኔን ፡ እኔ ፡ አልመራውም እኔነቴን ፡ እኔ ፡ አልወሰንኩም እኔ ፡ የእኔ ፡ አይደለሁም (፪x) ይሁና ፡ አንተ ፡ ያሰብክልኝ ይሁና ፡ የወደደክልኝ ይሁና ፡ የመረጥክልኝ ይሁን ፡ አሜን ፡ ይሁንልኝ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.