Loading
ጥንቅቅ ፡ አድርጐ ፡ ስራዬን ፡ ሰራልኝ፡ (ተፈፀመ) እዳዬን ፡ በደሙ ፡ አወራረደልኝ ፡ (ተፈፀመ) እውነትና ፡ ምሕረቱም ፡ ተስማሙልኝ ፡ (ተፈፀመ) ዘላለመ ፡ በርሱ ፡ ቀን ፡ ተወሰነልኝ ፡ (ተፈፀመ) የማረፊያ ፡ አረገው ፡ ዘላለሜን ፡ የማረፍያ ፡ አረገው (፫x) የደም ፡ ላብ ፡ እያላበው ፡ ፍቅር ፡ ግድ ፡ ስላለው (፪x) እንወደው ፡ ዘንድ ፡ እንኳ ፡ ደምግባት ፡ እስኪያጣ ፡ (ተፈፀመ) የህማም ፡ ሰው ፡ ሆነ ፡ በደዌ ፡ ተመታ ፡ (ተፈፀመ) እንዲህ ፡ ባለመውደድ ፡ እንዲህ ፡ ባለፍቅር ፡ (ተፈፀመ) እራሱን ፡ አሳየኝ ፡ አምኜው ፡ እንድኖር ፡ (ተፈፀመ) የማረፊያ ፡ አረገው ፡ ዘላለሜን ፡ የማረፍያ ፡ አረገው (፫x) የደም ፡ ላብ ፡ እያላበው ፡ ፍቅር ፡ ግድ ፡ ስላለው (፪x) አብ ፡ አስቀድሞ ፡ በልጁ ፡ ወሰነኝ ፡ (ተፈፀመ) ወስኖም ፡ መረጠኝ ፡ ሊያፀድቀኝ ፡ (ተፈፀመ) የቃሉን ፡ ብርሃን ፡ በልቤ ፡ አበራው ፡ (ተፈፀመ) አድራሻዬን ፡ ሊያደርግ ፡ በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ (ተፈፀመ) የደስታ ፡ አረገው ፡ ዘላለሜን ፡ የደስታ ፡ አረገው (፪x) የእፎይታ ፡ አረገው ፡ ዘላለሜን ፡ የእፎይታ ፡ አረገው (፪x) የደም ፡ ላብ ፡ እያላበው ፡ ፍቅር ፡ ግድ ፡ ስላለው (፪x) ተፈፀመ ፡ ተፈፀመ ፡ ተፈፀመ ፡ ተፈፀመ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.