Loading
ያ ፡ ሰነፍ ፡ ቢመስለው ፡ ያወቀ ከአባቱ ፡ እቅፍ ፡ ወጥቶ ፡ ወደቀ ሄደና ፡ እንዳሻው ፡ እንደልቡ እስኪረዳ ፡ እንደጣለ ፡ ክብሩን ተመልሶ ፡ መጣ ፡ በሀዘን ብሎ ፡ እንደባሪያው ፡ እንኳ ፡ ብሆን መመለሱን ፡ ያየም ፡ አባቱ አቀፈው ፡ ልክ ፡ እንደበፊቱ አዝ፦ ኧረ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ኧረ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ኧረ እያሳየ ፡ እየተገበረ (፪x) ይቺ ፡ ሴት ፡ ኃጢአተኛ ፡ ናት ህግ ፡ አለህ ፡ አንተም ፡ ፍረድባት እያሉ ፡ ላመጧት ፡ ለዚያች ፡ ነፍስ ጠበቁ ፡ ምን ፡ እንደሚመልስ እርሱ ፡ ግን ፡ እውነቱን ፡ ተናገረ ሁሉም ፡ ራሱን ፡ እንዲያይ ፡ አረገ የእሷንም ፡ ፍርዷን ፡ አንስቶላት አትድገሚው ፡ ልጄ ፡ ሂጂ ፡ አላት አዝ፦ ኧረ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ኧረ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ኧረ እያሳየ እየተገበረ (፪x) ሁሉ ፡ እንዲድን ፡ አንዷ ፡ እንዳትጠፋ ቢገደው ፡ ያ ፡ መልካም ፡ እረኛ በረት ፡ ያሉትን ፡ ይተውና ይሄዳል ፡ እሷኑ ፡ ፍለጋ ያሰማታል ፡ ድምጹን ፡ አውጥቶ በእቅፉ ፡ ሊያስገባት ፡ ጓጉቶ ነፍሱን ፡ ስለበጐቹ ፡ ያኖረው እውነተኛ ፡ ፍቅር ፡ እርሱ ፡ ነው አዝ፦ ኧረ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ኧረ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ኧረ እያሳየ እየተገበረ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.