Loading
ስለ ፡ ዛሬ ፡ የምን ፡ ታውቂያለሽ ፡ ቢሉኝ አንድ ፡ ነገር ፡ አንድ ፡ መልስ ፡ አለኝ በእውነት ፡ በእርግጠኛነት አለ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ስለ ፡ ነገስ ፡ ምን ፡ ታውቂያለሽ ፡ ቢሉኝ አንድ ፡ ነገር ፡ አንድ ፡ ዕውቀት ፡ አለኝ በእውነት ፡ በእርግጠኛነት አለ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት በየማለዳው ፡ የምረዳው ዕለት ፡ በዕለት ፡ የሚታይ ፡ እውነት (፪x) እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ ሌለ እግዚአብሔር ፡ ቸር ፡ እንደሆነ (፪x) ቸር ፡ ባይሆን ፡ ባለ ፡ ምህረት እኔ/አንዷ ፡ ነበርኩ ፡ ከሚጠፉት (፪x) ለክፉዎችም ፡ ቸር ፡ ለማያመሰግኑት ለሚወዱትም ፡ ቸር ፡ ለሚያምኑበት (፪x) ያለጠፋሁት ፡ በምን ፡ ምክኒያት ከቦኝ ፡ እንጂ ፡ የአንተ ፡ ምህረት እያለፈ ፡ እየተከተለኝ ክፉዉን ፡ ሁሉ ፡ ጥግ ፡ አስያዘልኝ የደረስክለት ፡ ያውራ ፡ እስኪ ፡ ያውራ ደግነትህን ፡ ይመስክር በአንተ ፡ የቀናለት ፡ አሃ ሕይወቱ ፡ መስመር (፪x) አልጣለኝም ፡ ደጋግ ፡ እጆችህ ፍቅር ፡ ናቸው ፡ ዛሬም ፡ ዓይኖችህ ለዘለዓለም ፡ ቤትህ ፡ እኖራለሁ ወደኸኛል ፡ እስከ ፡ መጨረሻው የደረስክለት ፡ ያውራ ፡ እስኪ ፡ ያውራ ደግነትህን ፡ ይመስክር በአንተ ፡ የቀናለት ፡ አሃ የሕይወቱ ፡ መስመር (፪x) ስለ ፡ ዛሬ ፡ የምን ፡ ታውቂያለሽ ፡ ቢሉኝ አንድ ፡ ነገር ፡ አንድ ፡ መልስ ፡ አለኝ በእውነት ፡ በእርግጠኛነት አለ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት ስለ ፡ ነገስ ፡ ምን ፡ ታውቂያለሽ ፡ ቢሉኝ አንድ ፡ ነገር ፡ አንድ ፡ ዕውቀት ፡ አለኝ በእውነት ፡ በእርግጠኛነት አለ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት በየማለዳው ፡ የምረዳው ዕለት ፡ በዕለት ፡ የሚታይ ፡ እውነት (፪x) እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ ሌለ እግዚአብሔር ፡ ቸር ፡ እንደሆነ (፪x) ቸር ፡ ባይሆን ፡ ባለ ፡ ምህረት እኔ/አንዷ ፡ ነበርኩ ፡ ከሚጠፉት (፪x) ለክፉዎችም ፡ ቸር ፡ ለማያመሰግኑት ለሚወዱትም ፡ ቸር ፡ ለሚያምኑበት (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.