Loading
አዝ፦ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ማረኝ ፡ አቤቱ ፡ ከመዓቱ (፪x) እንደሎጥ ፡ አድነኝ ፡ እንደኖህ ፡ አድነኝ አንደበቴ ፡ ረክሶ ፡ ሰላሜን ፡ ነጠቀኝ ስንዴነቴን ፡ እንጃ ፡ እንክርዳድ ፡ ብቻ ፡ ነኝ (፪x) አዝ፦ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ማረኝ ፡ አቤቱ ፡ ከመዓቱ (፪x) ጌታ ፡ ሆይ ፡ አየሁኝ ፡ ጊዜ ፡ ያሳይ ፡ የለ ያ ፡ ሁሉ ፡ ግለቴ??? ፡ ተሟጦ ፡ የታለ ቀኑን ፡ ሙሉ ፡ ልቤ ፡ አንተን ፡ እንዳላለ (፪x) አዝ፦ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ማረኝ ፡ አቤቱ ፡ ከመዓቱ (፪x) ቃልህን ፡ ህግህን ፡ እግሬ ፡ ስር ፡ ጥያለሁ እንደ ፡ ሥጋ ፡ ፈቃዴም ፡ እመላለሳለሁ ማረኝ ፡ እንደገና ፡ እማጸንሃለሁ (፪x) አዝ፦ ማረኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ማረኝ ፡ አቤቱ ፡ ከመዓቱ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.