Loading
አዝ፦ ድል ፡ በድል ፡ ጐዳና (፪x) ክርስቲያን ፡ አሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ አለንና (፪x) ያን ድቅድቅ ጨለማ የሞትን ሸለቆ ታገለው ክርስቲያን የእምነት ትጥቁን ታጥቆ አሻፈረኝ ብሎ ለእርሱ ላይረታ በድል ጥሎት ወጣ በጌታው መከታ አዝ:- ድል በድል ጎዳና ድል በድል ጎዳና ክርስቲያን ፡ አሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ አለንና (፪x) የጥሻው ጨለማ ብርሃን ወጣበት ክርስቲያን በእምነት ሰይፍ አንዴ ቢዘምትበት የማጥመጃው ሜዳ በደም አጥለቅልቆ ሕይወትን ዘራበት እንዲበቅል አውቆ አዝ:-ድል በድል ጎዳና ድል በድል ጎዳና ክርስቲያን ፡ አሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ አለንና (፪x) ጋሻ ጦሩ መንፈስ ፍላጻው እምነቱ ማን ሊቋቋመው ያን ክንደ ብርቱ ሊያጠምዱት ሊያስቀሩት አጥብቀው ቢጥሩ ከአምላኩ ደም ቅጥር አልነቀለም እግሩን አዝ:-ድል በድል ጎዳና ድል በድል ጎዳና ክርስቲያን ፡ አሸነፈ ፡ ኢየሱስ ፡ አለንና (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.