Loading
አለምን እንዳላይ አይኔን ተቆጣጠር ቀስ በቀስ እንዳልሄድ ወደ አታላይ ሃገር አንተ ብቻ እንድትሆን ማርና ወተቴ በእግርህ ስር እንድኖር ይሄ ነው ፀሎቴ ዝናም ከበሬታም ይጠፋሉ ፈጥነው አይደለም ነዋሪ ሃብትም እንደ ጢስ ነው ዘለአለም ነዋሪ ኢየሱስ ብቻ ነው መንፈሳዊ አይኖቼን ክፈታቸውና ልመልከት ጌታ ሆይ ደጉን እንደገና የጥንቱን ፍቅሬን ዳግም ብታለብሰኝ አያለሁ አጥርቼ ጉምም አይሸፍነኝ ዝናም ከበሬታም ይጠፋሉ ፈጥነው አይደለም ነዋሪ ሃብትም እንደ ጢስ ነው ዘለአለም ዘላቂ ኢየሱስ ብቻ ነው አተርፍ ባይ አጉዳይ መሆን ያስፈራኛል ከአንተ ጋር መሆኑ እጅግ ያዋጣኛል ህይወት መች ይሰጣል ወርቅ ቢያብረቀርቅ ቅብዝብዝ ይሆናል ሰው ከአንተ ቤት ሲርቅ ዝናም ከበሬታም ይጠፋሉ ፈጥነው አይደለም ነዋሪ ሃብትም እንደ ጢስ ነው ዘለአለም ዘላቂ ኢየሱስ ብቻ ነው የሰጠኅኝን ግብ እንዳልጥለው ወዲያ እንዳልገባ ሲኦል ከህይወት በስቲያ ይቅርብኝ እንግዲህ ብናኙ ግሳንግስ ልኑር በአንተ ጥላ ልቤን ለአንተ ላፍስስ ዝናም ከበሬታም ይጠፋሉ ፈጥነው አይደለም ነዋሪ ሃብትም እንደ ጢስ ነው ዘለአለም ነዋሪ ኢየሱስ ብቻ ነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.