Loading
አዝ፦ ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲሰራ አየነው ፡ ምርኮው ፡ ላይ ፡ ግርማው ፡ ሲያበራ የኃጢአት ፡ መጋረጃን ፡ በደሙ ፡ ቀደደ ከሳሻችን ፡ አፍሮ ፡ ወድቆ ፡ ሰገደ ይከሰን ፡ የነበረው ፡ የእዳ ፡ ጽሕፈት በደሙ ፡ ተደምስሷል ፡ በጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሞት ቀንበራችን ፡ ተሰብሮ ፡ አርነት ፡ ወጥተናል ጠላቶች ፡ የነበርነው ፡ በፀጋው ፡ ቀርበናል አዝ፦ ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲሰራ አየነው ፡ ምርኮው ፡ ላይ ፡ ግርማው ፡ ሲያበራ የኃጢአት ፡ መጋረጃን ፡ በደሙ ፡ ቀደደ ከሳሻችን ፡ አፍሮ ፡ ወድቆ ፡ ሰገደ ከድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ወደሚደነቅ ፡ ብርሃን በጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሥራ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጠራን ተስፋችን ፡ ያከተመ ፡ ደካሞች ፡ ሳለን በዘመኑ ፡ ፍፃሜ ፡ በልጁ ፡ ዋጀን አዝ፦ ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲሰራ አየነው ፡ ምርኮው ፡ ላይ ፡ ግርማው ፡ ሲያበራ የኃጢአት ፡ መጋረጃን ፡ በደሙ ፡ ቀደደ ከሳሻችን ፡ አፍሮ ፡ ወድቆ ፡ ሰገደ አእላፋት ፡ መላዕክት ፡ አገልጋይ ፡ ሳያንሰው ስለጠፋው ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰዋው በኃጢአት ፡ ረግረግ ፡ ውስጥ ፡ ሰጥመን ፡ ለጠፋነው ሊታደገን ፡ ወደደ ፡ ጭንቀታችን ፡ ተሰማው አዝ፦ ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲሰራ አየነው ፡ ምርኮው ፡ ላይ ፡ ግርማው ፡ ሲያበራ የኃጢአት ፡ መጋረጃን ፡ በደሙ ፡ ቀደደ ከሳሻችን ፡ አፍሮ ፡ ወድቆ ፡ ሰገደ መንገድ ፡ ተዘጋጀልን ፡ ግዛቱ ፡ ልንገባ የከበደን ፡ ቀንበር ፡ ሆኗል ፡ እንደ ፡ ገለባ እንራመዳለን ፡ ሸክም ፡ ቀሎናልና ዕረፍትን ፡ ስላገኘን ፡ ሆነን ፡ በምሥጋና አዝ፦ ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሲሰራ አየነው ፡ ምርኮው ፡ ላይ ፡ ግርማው ፡ ሲያበራ የኃጢአት ፡ መጋረጃን ፡ በደሙ ፡ ቀደደ ከሳሻችን ፡ አፍሮ ፡ ወድቆ ፡ ሰገደ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.