Loading
ሃይለኛ/4 ሃይለኛ ነው ያንቺ ጌታ ሃይለኛ ነው ያንተ ጌታ ለማንም የማይረታ ሃይለኛ ነው የኔ ጌታ ሃይለኛ ነው የኛ ጌታ ለማንም የማይረታ ለማንም የማይረታ በማንም የማይረታ/4 ማንም በማይደርሰው በችግሬ ላይ እኔ አበቃ ስል አንተ አለው እያልከኝ ኑሮዬን ያጣፈጥክ እድሜዬን የቀጠልክ አንተ ምን ልትባል በእኔ አንደበት እንዲ ልበል ገናና/8 እቅም ባጣሽ ግዜ ዙሪያሽም ጨልሞ ማነው ያበረታሽ ባጠገብሽ ቆሞ ጌታ አይደል ያንቺ መከታ ሰላምሽ የህይወትሽ ደስታ እርሱን ምን ልትይው በፊቱ እስቲ ወድቀሽ እንዲ በይው ገናና/8 ሃይለኛ/4 ሃይለኛ ነው ያንቺ ጌታ ሃይለኛ ነው ያንተ ጌታ ለማንም የማይረታ ሃይለኛ ነው የኔ ጌታ ሃይለኛ ነው የኛ ጌታ ለማንም የማይረታ ለማንም የማይረታ በማንም የማይረታ/4 ጌታ የማይረታ ጌታ ነው የማይረታ/4 እስቲ ቆም ብለህ አንዴ አስተውለው ውርደትን በክብር የቀየረው ማነው ጌታ እኮ ያንተ መከታ ስላንተ ሁሌ ሚዋጋ እርሱን ምን ልትለው በፊቱ እስቲ ሰግደህ እንዲ በለው ገናና/8 ሰይፉ በእጁ ነው ይቆራርጣል መርሹም በእጁ ነው ፈጥኖ ያጠራል ኧረ ይሄን ጌታ ማን ሊችለው ሲሰራ ማነው ሚከለክለው እርሱ እኮ ኤልሻዳይ ነው/4 የኔን ጌታ ማን ይመስለዋል እየሱሴን ማን ይመስለዋል ጌታ ማን ይመስለዋል/8
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.