Loading
በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ያለው እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x) እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x) ሰማያትን ፡ በሃይሉ ፡ ያጸና በምክሩም ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ እሱ ፡ ገናና እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ ለዘላለም (፪x) አዝ፦በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ያለው እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ ልዩ ፡ ነው (፫x) እስረኛውን ፡ የፈታ ፡ ያከበረ ምስኪኑን ፡ ሰው ፡ በከፍታ ፡ ላይ ፡ ያኖረ የባርነትን ፡ በትር ፡ የሰበረው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) አዝ፦በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ በክብር ፡ ያለው እግዚአብሔር ፡ ለኔ ፡ ልዩ ፡ ነው (፫x) እግዚአብሔር ፡ በተቀደሰ ፡ መቅደሱ ፡ አለ ጨለማውን ፡ የለየ ፡ ቀኑን ፡ ብርሃን ፡ ይሁን ፡ ያለ ዙፋኑ ፡ በሰማይ ፡ ነው ፡ በሰማይ ፡ ነው ፡ ኦሃሃሃ እንደ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማነው (ያለ ፡ ማነው) (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.