Loading
እስኪ ፡ ይናገሩ ፡ የተሻገርኳቸው ፡ እነዚያ ፡ መንገዶች ፍቅርና ፡ ምሕረትህ ፡ የደጋገፈኝ ፡ እነዚያ ፡ ቀናቶች እስኪ ፡ ይናገሩ ፡ የተሻገርኳቸው ፡ እነዚያ ፡ መንገዶች በእሳት ፡ አምድ ፡ ደመና ፡ ክንድህ ፡ ያሳለፈኝ ፡ እነዚያ ፡ ቀናቶች ይበሉ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የለም ይበሉ እንደ ፡ ጌታ ፡ ያለ ፡ የለም X፪ ነፍሴ ፡ በእግዚአብሔር ፡ አምናለችና ፡ አታፍርም አምናለችና ፡ አታፍርም ትልቅነቱን ፡ ታውቃለችና ፡ አታፍርም ታውቃለችና ፡ አታፍርም ይረዳታል ፡ ያግዛታል ፡ ከለላዋም ፡ ሆኖላታል ይረዳታል ፡ ያግዛታል ፡ ማዳኑንም ፡ ያሳያታል እላለሁ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የለም እላለሁ እንደ ፡ ጌታ ፡ ያለ ፡ የለም X፪ ሁኔታ ፡ እየመጣ ፡ ሲያነጋግረኝ ሲያነጋግረኝ የዛሬውስ ፡ መውጫሽ ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ ቢለኝ ምን ፡ ይሆን ፡ ቢለኝ X፪ አሄ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ይዤ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ሆናለሁ አሄ ፡ እረድኤቴ ፡ ጋሻ ፡ ሆኖልኝ ፡ እያየሁ አሄ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ይዤ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ሆናለሁ አሄ ፡ የከፍታዬ ፡ ሰይፍ ፡ ሆኖልኝ ፡ እያየሁ አሄ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ይዤ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ሆናለሁ አሄ ፡ ነገሬን ፡ በእጆቹ ፡ ይዞልኝ ፡ እያየሁ እላለሁ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የለም እላለሁ እንደ ፡ ጌታ ፡ ያለ ፡ የለም X፪
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.