Loading
"ማሜ ፡ አሁን ፡ እኮ ፡ ያለሽ ፡ እድል አባትሽህን ፡ ሄዶ ፡ ይቅርታ ፡ መጠየቅ ፡ ነው ። አዎ ፡ አውቃለሁ ። እንዴ ፡ ግን ፡ እኔ ፡ ይቅርታ ፡ እጠይቀዋለሁ? እንዴ ፡ ለምንድን ፡ ነው ፡ ሄደሽ ፡ ይቅርታ ፡ ማትጠይቄው? መጽሃፍ ፡ ቅዱስ ፡ እኮ ፡ ስለይቅርታ በጣም ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ የሚያስተምረን ። አዎ ፡ አውቃለሁ ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ የሚያስተምረን ። ግን ፡ እኮ ፡ አንዳንዴ ፡ አውቄ ፡ አጠፋለሁ ። አንዳንዴ ፡ ደግሞ ፡ ሳላውቅ ፡ አጠፋለሁ እየተሳሳትኩኝ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የተሸገርኩት ። አይ ፡ ልክ ፡ አይደለሽም ። አሁን ፡ ቀስ ፡ ብለሽ ፡ ሂጂና ፡ ይቅርታ ፡ መጠየቅ ፡ አለብሽ እንደተቀመጠ ፡ ቀስ ፡ ብለሽ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ሄደሽ ፡ ይቅርታ ፡ ጠይቂ ። ወይኔ ፡ ጉዴ ፡ እፈራለሁ ፡ እኮ ። እንዳይገርፈኝ ፡ ብዬ ፡ እኮ ፡ ፈርቼ ፡ ነው ። አትፍሪ ፡ አይዞሽ ። ሂጂ ፡ ሂጂ ፡ አይዞሽ ፡ አትፍሪ ።" ስለተሳሳትኩኝ ፡ ስላጠፋሁት አውቄም ፡ ሳላውቁም ፡ ሁሉ ፡ ላረኩት ጥፈተኝነቴ ፡ ገብቶኝ ፡ ይኸው ፡ ወጥቻለሁና ድጋሜ ፡ አላጠፋም ፡ ለዛሬም ፡ ይቅርታ (፪x) ይቅርታ (፪x) ፡ ይቅርታ (፬x) ይቅርታ (፪x) ፡ ይቅርታ (፬x) ያጠፋሸው ፡ ጥፋት ፡ በሙሉ ፡ ገብቶሻል ቶሎ ፡ ብለሽ ፡ መጥተሽ ፡ ይቅርታ ፡ ብለሻል ድጋሚ ፡ አታጥፌ ፡ እንጂ ፡ ልጄ እኔም ፡ በጣም ፡ እወድሻለሁ ነይ ፡ ልሳምሽ ፡ አንዴ ፡ ይቅር ፡ ብዬሻለሁ I love you (እወድሻለሁ) (፮x) I love you (እወድሻለሁ) (፮x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.