Loading
በእኔ ላይ ምህረቱ ነው የበላይ ትርጉም አይገኝም ስለእርሱ ምህረት ፈጽሞም አያልቅም ቢባል ቢባልለት ልገልጸው አልችልም እኔም አቅቶኛል በእኔ ላይ ምህረቱ እጅግ በዝቶልኛል በእኔ ላይ ምህረቱ ነው የበላይ ከተወለድኩበት እስክ አሁን ቀን ድረስ በዚህች በምድር ላይ ቆሜ ስመላለስ በህይወቴ ዘመን የበዛው ጥበቃ ነፍሴን አሳረፋት ምሳቀቋ በቃ በእኔ ላይ ጥበቃው ነው የበላይ ለውድ ድር ብዬ ፍቅሩን አላቀርብም የአምላክ ፍቅር ከሰው ምድቡም አይግጥምም ይእርሱስ የተለየ መውደዱም ልዩ ነው ብእኔ ላይ የበላይ የአምላኬ ፍቅር ነው የኢየሱስ ፍቅር ነው በእኔ ላይ ፍቅሩ ነው የበላይ ቆጥቦ ሰስቶ ወስኖ አይሰጠኝም ቸር ነውና እርሱ ደጅ አያስጠናኝም ለህይወቴ ዘመን የሚያስፈልገኝን በኔ ላይ ይሞላል ቸር ነው አይነሳኝም ቸር ነው አይነጥቀኝም ብእኔ ላይ ቸርነቱ ነው የበላይ ከሞትና ሲዖል ወጣሁ ከሰቀቀን በጣም ተደላደልኩ ጌታን ያገኘሁ ቀን በህይወት መዝገብ ላይ ስሜን አሰፈረ ሰይጣን ላያገኘኝ ዘላልም አፈረ ዘላለም ከሰረ በእኔ ላይ ማዳኑ ነው የበላይ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.