Loading
የሕይወት ፡ ሚስጥር ፡ ሳይገባቸው ፡ ሲከተሉ ፡ ለእንጀራቸው አልተስማሙም ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ተመለሱ ፡ ወደ ፡ ኋላ እኔስ ፡ በርቶልኛል ፡ መዳን ፡ ሆኖልኛል ሕይወት ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ኢየሱስ ፡ የለህ ፡ አቻ አዝ፦ ምንም ፡ ላላገኝ ፡ ከአንተ ፡ ርቄ ፡ ላይሆንልኝ ጥሜ ፡ ላይረካ ፡ የዓለም ፡ ኑሮ ፡ ላይፈይደኝ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደ ፡ አንተ ለእኔ ፡ የሚሆን ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አላየሁኝ (፪x) መድኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ የሚመስልህ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ መከታዬ ፡ ጋሻዬ ፡ ነህ ፡ ከለላዬ ከአንተ ፡ አልለይም ፡ ሌላው ፡ አይሆንልኝም የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለህ ፡ ጥሜን ፡ ታረካለህ አዝ፦ ምንም ፡ ላላገኝ ፡ ከአንተ ፡ ርቄ ፡ ላይሆንልኝ ጥሜ ፡ ላይረካ ፡ የዓለም ፡ ኑሮ ፡ ላይፈይደኝ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደ ፡ አንተ ለእኔ ፡ የሚሆን ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አላየሁኝ (፪x) ከአንተ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ተመችቶኛል ፡ ኢየሱሴ ፡ ጉያህ : ሞቆኛል በፍቅርህ ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሳብከኝ ፡ እስከሞት ፡ ድረስ ፡ የወደድከኝ በቃ ፡ ወስኛለሁ ፡ አንተን ፡ መርጫለሁ እርስቴ ፡ ነህ ፡ ብያለሁ ፡ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ አዝ፦ ምንም ፡ ላላገኝ ፡ ከአንተ ፡ ርቄ ፡ ላይሆንልኝ ጥሜ ፡ ላይረካ ፡ የዓለም ፡ ኑሮ ፡ ላይፈይደኝ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደ ፡ አንተ ለእኔ ፡ የሚሆን ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አላየሁኝ (፪x) ኢየሱስ ፡ ሕይወቴን ፡ አብርተሃል ፡ እኔነቴን ፡ ለውጠሃል አልለይህም ፡ ወድሃለሁ ፡ ከአንተ ፡ ውጪ ፡ ጨለማ ፡ ነው ግዛኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ልስገድ ፡ ጠዋት ፡ ማታ ነፍሴን ፡ የተቤዠህ ፡ አንተው ፡ ትሻሃለኛለህ አዝ፦ ምንም ፡ ላላገኝ ፡ ከአንተ ፡ ርቄ ፡ ላይሆንልኝ ጥሜ ፡ ላይረካ ፡ የዓለም ፡ ኑሮ ፡ ላይፈይደኝ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደ ፡ አንተ ለእኔ ፡ የሚሆን ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ አላየሁኝ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.