Loading
ዓለሙም ፡ ምኞቱም ፡ አንድ ፡ ላይ ፡ ጠፊ ፡ ነው (፪x) ዘለዓለም ፡ የሚያኖር ፡ የጌታን ፡ ፍቃዱን ፡ ማድረግ ፡ ነው (፪x) አትታለል ፡ ልቤ ፡ በሚያብለጨልጨው ከክፋቱ/ከአመጹ ፡ ጋራ ፡ ይህ ፡ ዓለም ፡ ጠፊ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ዓለም ፡ ዓለም ፡ አታልይ ፡ ናት (፪x) እውነት ፡ ሕይወትና ፡ መንገድ ፡ ጌታ ፡ ኦ ፡ ለታመኑበት (፪x) ከእሳት ፡ ተጠብቆ ፡ ለሚቆየው ፡ ዓለም (፪x) ነፍሴ ፡ አትጓጊለት ፡ በፍፁም ፡ ይቅርብሽ ፡ ግድየለም (፪x) ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሕይወት ፡ እርሱ ፡ ብቻ ከእሳት ፡ ከጨለማው ፡ በእምነት ፡ ማምለጫ (፪x) አዝ፦ ዓለም ፡ ዓለም ፡ አታልይ ፡ ናት (፪x) እውነት ፡ ሕይወትና ፡ መንገድ ፡ ጌታ ፡ ኦ ፡ ለታመኑበት (፪x) ሕይወትና ፡ ተስፋ ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ (፪x) በእውነት ፡ ለታመኑበት ፡ የሚሰጥ ፡ ከጌታ (፪x) ይህን ፡ ያስተዋለ ፡ ጌታን ፡ ሙጥኝ ፡ ይላል ከዚህ ፡ ዓለም ፡ እድፈት ፡ እራሱን ፡ ያነጿል (፪x) ዓለምን ፡ አትርፎ ፡ ሰው ፡ ነፍሱን ፡ ቢያጐድላት ከቶ ፡ ምን ፡ ሊጠቅመው ፡ ሁሌ ፡ ላይኖርባት ብልጭልጯን ፡ ንቆ ፡ እንደ ፡ ቃሉ ፡ የኖረ እርሱ ፡ ነው ፡ ጠቢብ ፡ ሰው ፡ ያ ፡ ነው ፡ የተማረ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.