Loading
አዝ፦ ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል ምሕረቱ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል የድሃ ፡ አደግ ፡ ወዳጅ ፡ የምስኪን ፡ ጓደኛ ማን ፡ እንደ ፡ ኢየሱሴ ፡ ታማኝ ፡ ሚስጥረኛ መድኃኒቴ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ አመልከዋለሁ ምሥጋናም ፡ ክብርም ዝማሬም ፡ ለእርሱ ፡ ነው (፮x) አዝ፦ ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል ምሕረቱ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል ኃጥያተኛ ፡ ብሎ ፡ ሁሉም ፡ ተፀይፏት ያለርህራሄ ፡ በድንጋይ ፡ ሊወግሯት እንዳትሞት ፡ የሚፈልግ ፡ ተገኘ ፡ የሚወዳት ጥበብን ፡ ተናግሮ ፡ ከጨካኙ ፡ አዳናት አትሞቺም ፡ አላት(፭x) አዝ፦ ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል ምሕረቱ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል የአንዲቷ ፡ ነፍስ ፡ ጌታን ፡ በጣም ፡ ግድ ፡ ብሎት በሰማሪያ ፡ መንገድ ፡ አለፈ ፡ ሊያድናት የነፍሷን ፡ ጥያቄ ፡ የውስጧን ፡ ፈታላት የሕይወትን ፡ ውኃ ፡ አፍለቀለቀላት አትጠሚም ፡ አላት(፭x) አዝ፦ ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል ምሕረቱ ፡ ሁልጊዜ ፡ ያስደንቀኛል ሁልጊዜ ፡ ያስገርመኛል አቤቱ ፡ ጌታዬ ፡ ሁሌ ፡ አከብርሃለሁ ፍቅርህን ፡ እያሰብኩ ፡ እገዛልሃለሁ ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ ንገሥ ፡ ለዘለዓለም በሰማይ ፡ በምድር ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ የለም (፮x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.