Loading
አላሳልፈኝ ፡ ያለው ፡ የብረት ፡ መዝጊያው ኧረ ፡ እንዴት ፡ ተከፈተ ፡ አሁን ፡ በጊዜው (፪x) ባለስልጣኑን ፡ ጌታ ፡ በእኔ ፡ ሲያየው ለመከፈት ፡ መነካት ፡ አላስፈለገው (፪x) አልፈራም ፡ ነገን ፡ ምን ፡ እሆን ፡ ብዬ እኖራለሁ ፡ በእርሱ ፡ ተደላድዬ አልሰጋም ፡ ነገን ፡ ምን ፡ እሆን ፡ ብዬ እኖራለሁ ፡ በእርሱ ፡ ተደላድዬ ኧረ ፡ ምን ፡ ችግር ፡ አለ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ (፪x) ኧረ ፡ ምን ፡ ችግር ፡ አለ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ አያለ ኧረ ፡ ምን ፡ ችግር ፡ አለ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ እሄዳለሁኝ ፡ ገና ፡ አላቋርጥም በእኔ ፡ ያለው ፡ እርሱ ፡ ፍፁም ፡ አይደክምም (፪x) በኃይልና ፡ በብርታት ፡ በእኔ ፡ ሳይሆን በመንፈሱ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ችላለሁ ፡ ሁሉን (፪x) በእርሱ ፡ ታምኜ ፡ ምን ፡ እሆናለሁ በትከሻው ፡ መሃል ፡ ላይ ፡ በክብር ፡ አድራለሁ (፪x) ኧረ ፡ ምን ፡ ችግር ፡ አለ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ (፪x) ኧረ ፡ ምን ፡ ችግር ፡ አለ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ አያለ ኧረ ፡ ምን ፡ ችግር ፡ አለ ጌታዬ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ እስቲ ፡ ልናገር ፡ ስለዚህ ፡ ጌታ ፡ አሃ የጠላቴን ፡ ትጥቅ ፡ አቤት ፡ ሲያስፈታ (፫x) አደራረጉ ፡ ከሰው ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ኦሆ የእኔ ፡ እኮ ፡ ጌታ ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው ፤ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው (፪x) ቀን ፡ በቀን ፡ እኔ ፡ ማየው ፡ ቀን ፡ በቀን የሚያሳየኝ ፡ ጉድ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ቀን ፡ በቀን ከትላንቱ ፡ ይልቅ ፡ ዛሬ ፡ በልጧል የማዳን ፡ እጁ ፡ ለእኔ ፡ ቀርቧል (፪x) ከትላንቱ ፡ ይልቅ ፡ ዛሬ ፡ በልጧል የማዳን ፡ እጁ ፡ ለእኔ ፡ ቀርቧል (፪x) በተዐምር ፡ እወጣለሁ ፡ በተዐምር ፡ እገባለሁ የታመንኩበት ፡ ጌታዬ ፡ ተዐምረኛ ፡ ነው (፪x) አሁን ፡ አሁንማ ፡ ብሷል ፡ አሁን ፡ አሁን (፪x) እኔም ፡ አምነዋለሁ ፡ እርሱም ፡ ይሰራል ከተዐምራቱ ፡ እኔን ፡ ያጠግበኛል (፪x) እኔም ፡ አምነዋለሁ ፡ እርሱም ፡ ይሰራል ከተዐምራቱ ፡ እኔን ፡ ያጠግበኛል (፪x) እስቲ ፡ ልናገር ፡ ስለዚህ ፡ ጌታ ፡ አሃ የጠላቴን ፡ ትጥቅ ፡ አቤት ፡ ሲያስፈታ (፫x) አደራረጉ ፡ ከሰው ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ ኦሆ የእኔ ፡ እኮ ፡ ጌታ ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.