Loading
የእርሱን ፡ ጥበብ ፡ ታላቅነት ምስክር ፡ ነው ፡ የሰራው ፡ ፍጥረት (፪x) ሁሉም ፡ ያውራ ፡ ይተርክለት ቃሉን ፡ ሥራውን ፡ ይጨዋወቱት (፪x) እኔስ ፡ ላውራለት ቅኔን ፡ ልቀኝለት ቅኔን ፡ ልቀኝለት (፪x) እስቲ ፡ ላነሳሳው (፫x) ፡ እስቲ ፡ ልናገረው የጌታዬ ፡ ሥራው ፡ በሙሉ ፡ ድንቅ ፡ ነው ሥሙን ፡ እየጠራሁ ፡ እስቲ ፡ ልወድሰው አያልቅበት ፡ እርሱ ፡ ብቻውን ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x) የምድር ፡ ዕፅዋት ፡ የምድር ፡ እንስሳት ለቅጽበት ፡ አይቆሙም ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ ምህረት (፪x) የአቀማመጥቸው ፡ አቤት ፡ የውበታቸው ቢታቱ ፡ ቢታዩ ፡ የማይጠገቡ ፡ ናቸው (፪x) አምልኮው ፡ ለአንተ ዝማሬው ፡ ለአንተ ዕልልታው ፡ ለአንተ ጭብጨባው ፡ ለአንተ (፪x) እስቲ ፡ ላነሳሳው (፫x) ፡ እስቲ ፡ ልናገረው የጌታዬ ፡ ሥራው ፡ በሙሉ ፡ ድንቅ ፡ ነው ሥሙን ፡ እየጠራሁ ፡ እስቲ ፡ ልወድሰው አያልቅበት ፡ እርሱ ፡ ብቻውን ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x) ሁሉን ፡ የሚችለው ፡ የአምላክ ፡ እስትንፋስ ፡ ፈጠረኝ አበጃጀኝና ፡ ሕይወትንም ፡ ሰጠኝ (፪x) የፈጠርከኝ ፡ ጌታ ፡ እኔም ፡ አከብርሃለው ስለ ፡ አንተ ፡ ላወራ ፡ ይኸው ፡ መጥቻለሁ (፪x) አምልኮው ፡ ለአንተ ዝማሬው ፡ ለአንተ ዕልልታው ፡ ለአንተ ጭብጨባው ፡ ለአንተ (፪x) እስቲ ፡ ላነሳሳው (፫x) ፡ እስቲ ፡ ልናገረው የጌታዬ ፡ ሥራው ፡ በሙሉ ፡ ድንቅ ፡ ነው ሥሙን ፡ እየጠራሁ ፡ እስቲ ፡ ልወድሰው አያልቅበት ፡ እርሱ ፡ ብቻውን ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x) አምልኮው ፡ ለአንተ ዝማሬው ፡ ለአንተ ዕልልታው ፡ ለአንተ ጭብጨባው ፡ ለአንተ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.